You are currently viewing አሳዛኝ ዜና! በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማክሰኝት ከተማ ትጥቅ ለማስፈታት በሚል በተወሰደ የኃይል እርምጃ የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል። አሻራ ሚዲያ… ሰሜን አሜሪካ  በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማ…

አሳዛኝ ዜና! በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማክሰኝት ከተማ ትጥቅ ለማስፈታት በሚል በተወሰደ የኃይል እርምጃ የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል። አሻራ ሚዲያ… ሰሜን አሜሪካ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማ…

አሳዛኝ ዜና! በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማክሰኝት ከተማ ትጥቅ ለማስፈታት በሚል በተወሰደ የኃይል እርምጃ የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል። አሻራ ሚዲያ… ሰሜን አሜሪካ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ማክሰኝት ከተማ በሆቴል ውስጥ የነበሩ አምስት ፋኖዎችን በኃይል ትጥቅ ለማስፈታት መንግስታዊ ስምሪት የተሰጣቸው የጸጥታ አካላት ተኩስ መክፈታቸው ተገልጧል። ፋኖዎችም ትጥቅ ላለመፍታት እና ራሳቸውን ለመከላከል ሲሉ የአጸፋ ምላሽ መስጠታቸውን ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) የደረሱ መረጃዎች አመልክተዋል። በተመሳሳይ ከበባ ተደርጎ ተኩሱ የተከፈተው ሆቴል ላይ ስለነበር በውስጡ በነበሩ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱም ታውቋል። አሚማ ከጎንደር ዙሪያ ወረዳ ፋኖ የሽፈራው ማመጫ ሻለቃ አዛዥ ከሆኑት ከፋኖ ጓዴ ባንቲ ጋር ቆይታ አድርጓል። ሻለቃ ጓዴ ባንቲ እንደገለጹት ግንቦት 28/2014 ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ የጀመረው ተኩስ እስከ ምሽት 4 ሰዓት ድረስ መቀጠሉንም ተናግረዋል። በመንግስት ጥምር ኃይል በኩል ቦምብ እና ብሬን ጭምር እስከመጠቀም መደረሱ አሳዛኝ ስለመሆኑ የተናገሩት ሻለቃ ጓዴ አላማው ትጥቅ ማስፈታት ነው ብለዋል። “የሚፈለጉበት ነገር ስለመኖሩ የማውቀው ነገር የለኝም” ያሉት ሻለቃ ጓዴ ወንጀል ካለም በህግ አግባብ ተጠይቀው ትምህርት መውሰድ ነው የሚገባቸው እንጅ ዝም ብሎ እንደዚህ ሜዳ ላይ ማፈስና ትጥቅህን አውርድ ማለቱ አግባብነት ያለው አይመስለኝም ብለዋል። ጉዳዩ እንዲረግብ በሚል በእሳቸው ሻለቃ የሚመሩ ሌሎች የፋኖ አባላት በተኩሱ እንዳይሳተፉ፣ ይልቁንስ በያሉበት አርፈው እንዲቀመጡ አድርጌያለሁ ብለዋል። ትጥቅ እንዲፈቱ እና እጅ እንዲሰጡ በሚል ተኩስ” የተከፈተባቸው ፋኖዎችም:_ 1) ምክትል የሻለቃ መሪው ሹመት፣ 2) አቸነፍ አዳነ፣ 3) ደጀኔ፣ 4) መሳፍንት ጥላሁን እና 5) ወንዳወንድ የተባሉ ፋኖዎች ናቸው። ሻለቃ ጓዴ ሲቀጥሉ ለማዕከላዊ ጎንደር ዞን ሰላም እና ደህንነት ኃላፊ ለአቶ ዳኘ በመደወል ነገሩ እንዲበርድ ብጠይቅም “እጅ ይስጡ” ከማለት ውጭ ሊረዱን አልቻሉም ብለዋል። እጅ ሲሰጡ በአግባቡ ነው መስጠት ያለባቸው፣ ሽማግሌ ቀርቦ ለህግ እጃቸውን እንዲሰጡ ቢደረግ የሚል ሀሳብ ባነሳም አቶ ዳኘ አልተቀበሉኝም ሲሉም አክለዋል። የወረዳው ሰላም እና ደህንነት ኃላፊ አቶ ኤርሚያስም ፈቃደኛ አልሆኑም ሲሉ ተናግረዋል። በውስጥ ካሉት መካከል ምክትል ሻለቃ ሹመት አምባቸው ተመቶ “ቆስያለሁ፤ ለሚመለከተው አካል ንገርልኝ፤ አትርፉኝ፤ ህክምና አድርሱኝ” እያለ በስልክ ተገናኝተን ነበር፤ ምንም ፋታ ሊሰጡን አልቻሉም” ሲሉ ነው ሻለቃ ጓዴ የገለጹት። ይህ መንግስታዊ ጥምር ኃይል አትቅረቡ በማለት በማህበረሰቡ ላይም ከፍተኛ ድብደባ ፈጽሟል ሲሉ ወቅሰዋል። በመጨረሻም አሚማ የዞኑን ሰላም እና ደህንነት ኃላፊን አቶ ዳኘን ለማግኘት ያደረገው ጥረት ስልካቸው ባለመስራቱ አልተሳካም። የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ሰላም እና ደህንነት ኃላፊ አቶ ኤርሚያስንም በእጅ ስልካቸው በመደወል ያገኘናቸው ቢሆንም ምላሽ ለመስጠት አልፈቀዱም። አሚማ ግንቦት 29/2014 ያጣራው መረጃ እንዳመለከተው:_ 1) “ቆስያለሁ፤ አትርፉኝ” እያለ ጥሪ ሲያደርግ የነበረው የሽፈራው ማመጫ ሻለቃ ምክትል የሻለቃ አዛዥ ሹመት አምባቸው፣ 2) መሳፍንት ጥላሁን የተባለ የፋኖ አባል እና 3) አቶ በየነ ማንፍሮ የተባለ ለገበያ ከገጠር የሄደ አርሶ አደር ተገድለው ተገኝተዋል። የነበሩበት ሆቴል በአብሬጅ እና በቦምቦ እንዲቃጠል በመደረጉ አስከሬናቸው በእሳት ተበልቶ መገኘቱ ታውቋል። ሌላም አስከሬን ካለ በሚል በተቃጠለው ቤት ውስጥ እየተፈለገ መሆኑ ተገጧል። ትጥቅ ለማስፈታት ስምሪት ላይ ከነበሩ አካላት መካከልም አንድ የልዩ ኃይል ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል። በያዝነው የግንቦት ወር 2014 “መንግስት ህግ የማስከበር እርምጃ እየወሰድኩ ነው፤ ይህም የጠላቶቻችንን ቅስም የሰበረ ነው፤ ከእርምጃው በኋላም ሰላም ሰፍኗል” በሚል አንዳንድ አካባቢዎች በሰልፍ ሁሉ ድጋፋችሁን ግለጹልኝ በሚል እየተንቀሳቀሰ መሆኑ እያነጋገረ ነው። ብዙዎች ግን ህግ ማስከበር ሳይሆን በፋኖ ላይ ብሎም በአጠቃላይ አማራን አንገት ለማስደፋት በማሰብ የተከፈተ መንግስታዊ ጥቃት ነው በማለት እያገዙት ይገኛሉ። በዚህም በምዕራብ ጎጃም ዞን ሰሜን ሜጫ ወረዳ መርዓዊ ከተማ እና በእናሸንፋለን ቀበሌ እነ አርበኛ ዘመነ ካሴን አገኛለሁ በሚለው፣ በምስራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ፣ በየጁቤ ኮርክ፣ በሰሜን ወሎ ዞን ወልድያ ከተማ፣በደቡብ ወሎ ዞን ሀርቡ ከተማ እንዲሁም አሁን ደግሞ በጎንደር ማክሰኝት ላይ ፋኖዎችን ትጥቅ ለማስፈታት በሚል በከፈተው ተኩስ በተጠቀሱት አካባቢዎች በርካታ ፋኖዎችና ሌሎች ንጹሃን መገደላቸው፣ የቆሰሉ መኖራቸውና በብዙ ሽህዎች የሚቆጠሩ ፋኖዎችም ወደ ጫካ መግባታቸው ይታወቃል ሲል አሚማ ዘግቧል ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply