You are currently viewing አሳዛኝ ዜና! በምስራቅ ወለጋ ዞን በኪረሞ ወረዳ ሀሮ አዲስ ዓለም አማራዎች ላይ  በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት ተከፍቷል፤ የድረሱልን ጥሪም ቀርቧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ    ታህሳስ…

አሳዛኝ ዜና! በምስራቅ ወለጋ ዞን በኪረሞ ወረዳ ሀሮ አዲስ ዓለም አማራዎች ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት ተከፍቷል፤ የድረሱልን ጥሪም ቀርቧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ…

አሳዛኝ ዜና! በምስራቅ ወለጋ ዞን በኪረሞ ወረዳ ሀሮ አዲስ ዓለም አማራዎች ላይ በከባድ መሳሪያ የታገዘ ጦርነት ተከፍቷል፤ የድረሱልን ጥሪም ቀርቧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 14 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ ዞን በተለያዩ ወረዳዎች የሚኖሩ አማራዎች የክልሉ መንግስት ልዩ ኃይል የሚመራው ጦርነት በተለይም ከህዳር 9/2015 ጀምሮ የተከፈተባቸው መሆኑን በመግለጽ የድረሶልን ጥሪ ሲያሰሙ ሰንብተዋል። ይሁን እንጅ የሚመለከታቸው የፌደራሉ የመንግስት አካላት ስምሪት ባለመስጠታቸው ከአንገር ጉትን ውጭ መከላከያ አልገባም፤ አንገር ጉትን የገባው መከላከያም የሸኔ አጋር ከሆኑ የኦሮሞ ሚሊሾች ጋር በመሆን ከአንድ መቶ በላይ አማራዎችን አስሯል በሚል ነዋሪዎች አቤቱታ እያቀረቡበት ነው። ህዳር 9፣10፣11 እና 20/2015 4 ዙር በኪረሞ አማራ ላይ ጦርነት በመክፈት በርካቶችን የገደሉት፣ የረሸኑት፣ ያገቱት፣ ያቆሰሉት፣ የዘረፉት እና ከ52 ሽህ በላይ አማራዎችን ያፈናቀሉት የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ ኦነግ ሸኔ እና አጋሮቻቸው ታህሳስ 14/2015 በሀሮ አዲስ ዓለም ነዋሪዎች ላይ በቡድን መሳሪያ የታገዘ ጦርነት ጀምረዋል። ሀሮ አዲስ ዓለምን በአራት አቅጣጫዎች ከበው ያደሩት እነዚህ በዘር ተኮር ጥቃትና በጭካኔያቸው የተመሰከረላቸው ኃይሎች ታህሳስ 14/2015 ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ ጦርነት በመክፈት አማራዎችን እየገደሉ እና እያሳደዱ ይገኛሉ። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በከባድ መሳሪያ የታገዘው ጦርነት እንደቀጠለ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) በቀጥታ የሀሮ አዲስ ዓለም ነዋሪዎችን ሲያነጋግር አስፈሪ የሆነ የዲሽቃ እና የሌሎች የቡድን መሳሪያዎችን ድምጽ ይሰማ ነበር። የተደራጀ መንግስት መር ጦርነት የተከፈተበት ሀሮ አዲስ ዓለም ከነዋሪዎች ውጭ ከ100 ሽህ በላይ ተፈናቃዮች የሚኖሩበት አካባቢ ነው። በኪረሞ ወረዳ የሀሮ አዲስ ዓለም ቀበሌ መንገድ ከተዘጋበት 2 ዓመት አልፎታል፤ ህዳር 21/2015 እና ታህሳስ 11/2015 ጦርነት ተከፍቶበት እንደነበርም ይታወቃል። ከህዳር 9/2015 ጀምሮ የድረሱልን ጥሪ እያቀረቡ ያሉ የኪረሞ እና የሀሮ አዲስ ዓለም አማራዎች የደረሰላቸው የመንግስት አካል እንደሌለ በመግለጽ አሁንም የድረሱልን ተማጽኖ አቅርበዋል። የኦሮሚያ ክልል መንግስት በጸጥታ አካሉ የሚመራው አማራን ከኦሮሚያ የማጽዳት በቡድን መሳሪያ የታገዘው ጦርነት አሁንም ሀይ ባይ አላገኘም፤ ተጠያቂነት አልሰፈነም፤ ይልቁንስ ግድያው፣ አፈናው እና ማፈናቀሉ አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply