You are currently viewing አሳዛኝ ዜና! በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ቦቃ ቀበሌ በተስፋፊው፣ በጽንፈኛው፣ በጠባቡ፣ በሰው በላው እና አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከታገቱት 17 አማራዎች መካከል 11 የሚሆኑት በአሰቃቂ መልኩ በስ…

አሳዛኝ ዜና! በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ቦቃ ቀበሌ በተስፋፊው፣ በጽንፈኛው፣ በጠባቡ፣ በሰው በላው እና አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከታገቱት 17 አማራዎች መካከል 11 የሚሆኑት በአሰቃቂ መልኩ በስ…

አሳዛኝ ዜና! በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ቦቃ ቀበሌ በተስፋፊው፣ በጽንፈኛው፣ በጠባቡ፣ በሰው በላው እና አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከታገቱት 17 አማራዎች መካከል 11 የሚሆኑት በአሰቃቂ መልኩ በስለት ተገድለው ተገኙ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… መስከረም 7 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ቦቃ (ጉዲና ጅሬኛ) ቀበሌ በተስፋፊው፣ በጽንፈኛው፣ በጠባቡ፣ በሰው በላው እና አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና የዘር ማጥፋት ተባባሪዎቹ 17 አማራዎች መታገታቸውን አማራ ሚዲያ ማዕከል አሚማ መዘገቡ ይታወቃል። ታጋቾቹ ከኪረሞ ወረዳ ቦቃ ቀበሌ ጳጉሜ 2 ቀን 2013 አንድ አማራ በሽብር ቡድኑ ሲገደልባቸው ከቀያቸው ለቀው ወደ ኪረሞ ከገቡት መካከል 17 የሚሆኑት ናቸው። አንዳች የሰብአዊ እርዳታ የሚሰጣቸው የመንግስት አካል ባለማግኘታቸው በርሃብ ከምንሞት በሚል የተረፈ እህል ካለ ለማምጣት በማሰብ ነው ወደ ቀያቸው የተመለሱት። በተለይ ደግሞ ቀማኞቹ የደረሰ ማሽላቸውን እየቆረጡ አምጥተው ገበያ ላይ ሲሸጡ በማየታቸው ነበር በብስጭት መስከረም 6 ቀን 2014 ወደ ቀያቸው ያቀኑት። ያሰቡት ሳይሳካላቸው በድንገት ነበር በዘረኛው፣ በሰው በላው፣ በሰዋዊ አውሬው፣ በጠባቡ፣ በተስፋፊው፣ በጽንፈኛው እና አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና በተባባሪዎቹ እጅ የወደቁት። አሚማ ለማጣራት እንደሞከረውና ከአስከረፀን አንሽዎች እንደተረዳው ሚሊሻ፣ ልዩ ኃይል እና ፖሊስ ወደ ቦቃ ቀበሌ በማቅናት ዛሬ መስከረም 7 ቀን 2013 ከሰዓት በኋላ አስከሬን አንስቷል። ከታገቱት 17 አማራዎች መካከል 7 ሴቶች እና 4 ወንዶች በድምሩ 11 የሚሆኑት በቦቃ ቀበሌ በአንድ ቤት ውስጥ በአሰቃቂ መልኩ በስለት እና በእሳት ተገድለው ተገኝተዋል። አንገታቸው ክፉኛ ተገዝግዘው፣ አካላቸው በስለት ተወጋግቶ ለጊዜው ከተረፉት መካከልም 2 ሴት ህጻናት፣ ሁለት እናቶች እንዲሁም አንድ የተለቀቀ ህጻን ይገኙበታል። ለማስለቀቅ ጥረት እየሰሩ መሆናቸውን የነገሩን የኪረሞ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ደስታም ዛሬ ለማነጋገር አልፈቀዱም፤ የሚጠራ ስልካቸውን በተደጋጋሚ ዘግተዋል። በቦቃ ቀበሌ ኡልማይ አካባቢ ያሉ ከ3 ሽህ በላይ አማራዎችም ድረሱልን የሚል ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ ሚሊሾች ማቅናታቸው ተሰምቷል። ከእያንዳንዱ የጅምላ ግድያ በስተጀርባ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ብቻ ሳይሆን ተቋማትንና ከ19 ውስጥ 17 የሚሆኑ ቀበሌዎችን ለሽብር ቡድኑ ያስወረሩት በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ አካላት እጅ እንዳለበት በብዙዎች ዘንድ ጎልቶ እየተነገረ ያለ ጉዳይ ነው። አስከሬን ይዘው ወደ ኪረሞ ሲመለሱም ተኩስ እንደተከፈተባቸው የደረሰን መረጃ አመልክቷል፤ አጣርተን የምንመለስ ይሆናል። ነሃሴ 12 ቀን 2013 በቀላሉ የኢሰመጉ ሪፖርት እንዳመለከተው በትንሹ ከ300 በላይ የሚሆኑ አማራዎች በኪረሞ ወረዳ መርጋ ጅሬኛ ቀበሌና አካባቢው በጅምላ በመንጋ በስለት፣ በቡድን መሳሪያና በክላሽ መጨፍጨፋቸው ይታወሳል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply