You are currently viewing አሳዛኝ ዜና! በምስራቅ ወለጋ ዞን ጎብሰዮ ወረዳ  አኖ ከተማ በአማራዎች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ነው፤ በአንድ መጠለያ ከነበሩ ተፈናቃዮች በርካታ ስለመገደላቸው ተሰምቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/…

አሳዛኝ ዜና! በምስራቅ ወለጋ ዞን ጎብሰዮ ወረዳ አኖ ከተማ በአማራዎች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ነው፤ በአንድ መጠለያ ከነበሩ ተፈናቃዮች በርካታ ስለመገደላቸው ተሰምቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/…

አሳዛኝ ዜና! በምስራቅ ወለጋ ዞን ጎብሰዮ ወረዳ አኖ ከተማ በአማራዎች ላይ ጥቃት እየተፈጸመ ነው፤ በአንድ መጠለያ ከነበሩ ተፈናቃዮች በርካታ ስለመገደላቸው ተሰምቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 25 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪ ኦነጋዊያን በጥላቻ እና በሀሰት ትርክት ጎብጠው ንጹሃን አማራዎችን በጎዳና፣ በጫካ፣ በቤት ለቤት እና በመጠለያ እያሳደዱ መጨፍጨፋቸው ተሰምቷል። ጥር 25/2015 ከንጋቱ 12:30 ገደማ ጀምሮ በምስራቅ ወለጋ ዞን በጉብሰዮ ወረዳ በተለይም:_ 1) አኖ ከተማ እና 2) ባፈኖ በተባሉ አካባቢዎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኃይል በማሰማራት ከበባ በማድረግ እና ተኩስ በመክፈት አማራዎችን እየገደለ እና እያፈናቀለ መሆኑ ታውቋል። አኖ ከተማ ባለ የአማራ ሚሊሾች ካምፕ ላይ ድንገተኛ ተኩስ በመክፈት በርካቶችን መግደሉ ተሰምቷል። በኦሮሚያ ክልል መንግስት አካላት እየተደገፈ ማንነት ተኮር ጥቃት እየፈጸመ ያለው ኦነግ ሸኔ ወይም ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት እያለ የሚጠራው ወራሪ ቡድን ጎቡሰዮ ወረዳ በአኖ እና በባፈኖ ልዩ ትኩረት አድርጎ የከበባ ጦርነት ይክፈት እንጅ በተመሳሳይ አዋሳኝ በሆነው ምዕራብ ሸዋ ባኮቲቤን ለመያዝ ጊቤ ወንዝ አካባቢ ተኩስ መክፈቱ ተሰምቷል። ቡድኑ በጎብሰዮ፣ በአኖ፣ በስቡስሬ፣ በስሬ እና በባኮቲቤ በተለያዩ ጊዜያት በፈጸመው ማንነት ተኮር ጥቃት ተፈናቅለው በመጠለያ ያሉ አማራዎችን ትኩረት አድርጎ እየተንቀሳቀሰ መሆኑ ተገልጧል። አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ህዳር 27/2015 ከቀኑ 5 ሰዓት ጀምሮ እስከ ቀኑ 7 ሰዓት ድረስ በጎብሰዮ ወረዳ ከአኖ ከተማ በቅርብ ርቀት ባለችው ልዩ ስሟ ግሼ ቶርቤ በምትባል አካባቢ ባሉ የአማራ ተወላጅ የሆኑ ሚሊሾች ላይ ጥቃት ከፍቶ ግድያ እና ዝርፊያ መፈጸሙ ይታወሳል። በወቅቱም በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ ከተገደሉት መካከልም:_ 1) አቶ ሞህሙድ እንድሪስ፣ 2) አቶ ሰይድ እና 3) ሌላ አንድ ስሙ ያልታወቀ ሚሊሻዎች በመስተዳድሩ አሻጥር ጭምር መገደላቸው አይዘነጋም። ይህን ተከትሎ ህዳር 29/2015 በአስር መኪና የተሳፈሩ ተፈናቃይ አማራዎች በምዕራብ ሸዋ ዞን ባኮትቤን አቋርጠው ሸቦካ በተባለ አካባቢ ሲደርሱ በመስተዳድሩ እንዳያልፉ መከልከላቸው ይታወቃል። ጥር 25/2015 ጥቃቱ የተፈጸመባቸው ከቀያቸው ተፈናቅለው በከፍተኛ ችግር ላይ የነበሩ አማራዎች መሆናቸው ተሰምቷል። ቤት ለቤት እየዞረ፣ በመጠለያ ካምፕ፣ በጎዳና እና በየጫካው እየተንቀሳቀሰ ነው ወራሪ ቡድኑ ጭፍጨፋውን የፈጸመው ተብሏል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply