አሳዛኝ ዜና! በምዕራብ ወለጋ ዞን ግንቢ ወረዳ በቤታቸው የነበሩ እናት እና ልጅ በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በጥይት ተገደሉ፤ ከ300 በላይ አማራዎችም ከቀያቸው ተፈናቀሉ።…

አሳዛኝ ዜና! በምዕራብ ወለጋ ዞን ግንቢ ወረዳ በቤታቸው የነበሩ እናት እና ልጅ በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በጥይት ተገደሉ፤ ከ300 በላይ አማራዎችም ከቀያቸው ተፈናቀሉ።…

አሳዛኝ ዜና! በምዕራብ ወለጋ ዞን ግንቢ ወረዳ በቤታቸው የነበሩ እናት እና ልጅ በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በጥይት ተገደሉ፤ ከ300 በላይ አማራዎችም ከቀያቸው ተፈናቀሉ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ህዳር 30 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምዕራብ ወለጋ ዞን ግንቢ ወረዳ በ ቶሌ በተባለ ቀበሌ በቤታቸው የነበሩ እናት እና ልጅ በአማራዊ ማንነታቸው ብቻ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በጥይት ስለመገደላቸው ከቤተሰብና ከአካባቢው ነዋሪዎች የተገኘ መረጃ አመልክቷል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል ያነጋገራቸው የሟች ወ/ሮ ዘይነባ ሰይድ ባለቤት አቶ እንድሪስ ሰይድ አሊ ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ምሽት 1 ሰዓት ተኩል ላይ ከ30 በላይ የሚሆኑ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የመኖሪያ ቤታቸውን በመክበብ ክፈት በማለት በሩን ሲደበድቡ ሾልከው ስለማምለጣቸው ተናግረዋል። ይሁን እንጅ ወደ ቤት አነጣጥረው በመተኮስ ባለቤታቸውን ወ/ሮ ዘይነባ ሰይድ እና የ5 ዓመት ልጃቸውን ቶፊቅ እንድሪስን በጥይት ስለመግደላቸውም አውስተዋል። በወቅቱም ለፖሊሶችና ለቀበሌው የመስተዳድር አካላት እባካችሁ ድረሱልኝ፤ ቢያንስ ቁስለኛዋን ወደ ጤና ጣቢያ አድርሱልኝ በሚል ብጮህም አንድም የፀጥታ አካል ባለመድረሱ የባለቤቴ ህይወት አልፏል ነው ያሉት። የገዳዮችን ጭካኔ ሲገልፁም የ4 ወር ሴት ህጻን ልጅ የያዘችውን እመጫት ባለቤቴን ነው በጥይት ተኩሰው የገደሏትም ብለዋል። በአሁኑ ሰዓትም ከ300 በላይ አማራዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን የገለፁት አቶ እንድሪስ መንግስት በአካባቢው ተጨማሪ ኃይል በመላክ ህይወታቸውን እንዲታደጋቸው ጠይቀዋል። በዛሬው እለት አመሻሽም በቶሌ ቀበሌ ስልሳው በተባለ ጎጥ ላይ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ተኩስ ከፍተው እንደነበር የጠቆሙት ነዋሪው አሁን ላይ ከፍተኛ ስጋት ስለመኖሩ አስታውቀዋል። በተመሳሳይ ቀበሌ ህዳር 28 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 1:30 እስከ 2:00 ሰዓት ኦነግ ሸኔዎችና ተባባሪዎቻቸው 14 በሚሆኑ የአማራ ቤቶች ላይ አነጣጥረው በጥይት ደብድበዋል። ወጣት መሀመድ የተባለ አማራም ከቶሌ ቀበሌ ስልሳው ከተባለ ጎጥ በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ታፍኖ ከተወሰደ አንድ ወር ቢያልፈውም እስካሁን ያለበትን አድራሻና ሁኔታ ለማወቅ አልተቻለም ተብሏል። ከሁለት ወራት በፊት በግንቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ ጨፌ በተባለ ጎጥ ነዋሪ የሆኑት አቶ መሀመድ ሁሴን ለ5 ቀናት በኦነግ ሸኔ ከታገቱ በኋላ 100 ሽህ ብር፣ አቶ ያሲን ካሳ ደግሞ ከ3 ቀናት የእገታ ቆይታ በኋላ 60 ሽህ ብር በመክፈል ተለቀዋል። በጫካ ያሉ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች የአማራው ቤት የት እንደሆነ አያውቁም ያሉት ምንጫችን የመንግስት አካልን ጨምሮ ከአካባቢው ነዋሪዎችም መረጃ በመስጠት፣ስንቅና ትጥቅ በማቀበል በርካታ የጥፋት ተባባሪዎች እንዳሉ ጠቁመዋል። የኦሮሚያ ልዩ ሀይሎችም በኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች ላይ የጨከነ እርምጃ አይወስዱም ያሉት የአካባቢው ነዋሪ አንዳንዴ ሲያገኟቸውም በዝምታ አለፉ ላለመባል ወደላይ ተኩሰው ይመለሳሉ ብለዋል። ከሟች ባለቤት እና ከአካባቢው ነዋሪ ጋር የተደረገውን ቆይታ በአሚማ የዩቱብ አድራሻ የምናጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply