You are currently viewing አሳዛኝ ዜና! በሰሜን እና ደቡብ አቸፈር ወረዳዎች ውሀ እና መብራት ይሰጠን ብለው  ተቃውሞ ባሰሙ ወጣቶች ላይ ፖሊስ በተኮሰው ጥይት በወጣቶች እና ህፃናት ላይ የአካል ጉዳትና የህይወት እልፈ…

አሳዛኝ ዜና! በሰሜን እና ደቡብ አቸፈር ወረዳዎች ውሀ እና መብራት ይሰጠን ብለው ተቃውሞ ባሰሙ ወጣቶች ላይ ፖሊስ በተኮሰው ጥይት በወጣቶች እና ህፃናት ላይ የአካል ጉዳትና የህይወት እልፈ…

አሳዛኝ ዜና! በሰሜን እና ደቡብ አቸፈር ወረዳዎች ውሀ እና መብራት ይሰጠን ብለው ተቃውሞ ባሰሙ ወጣቶች ላይ ፖሊስ በተኮሰው ጥይት በወጣቶች እና ህፃናት ላይ የአካል ጉዳትና የህይወት እልፈት እንዲደርስ ማድረጉ ተሰማ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … መጋቢት 4 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በሰሜን እና ደቡብ አቸፈር ወረዳዎች ውሀ እና መብራት ይሰጠን ብለው ተቃውሞ ባሰሙ ወጣቶች ላይ ፖሊስ ጥይት በመተኮስ ጉዳት አድርሷል። በጥቃቱም በወጣቶች እና ህፃናት ላይ የአካል ጉዳትና የህይወት እልፈት እንዲደርስ ማድረጉ ተገልጧል። የወረዳው ፖሊስ በወጣቶች ላይ በከፈተው ተኩስ ሶስት ወጣቶች መመታታቸውን ምንጮች ገልጸዋል። በዚህም የ16 አመት ልጅ የሆነው ወጣት ኤርሚያስ አብየ በጥይት ተመቶ በጥበበ ጊዮን ሆስፒታል ኮማ ውስጥ ቆይቶ መጋቢት 4/2015 መሞቱ ታውቋል። በማዕከላዊ ጎንደር፣በምዕ/ጎጃም እና በአዊ ዞኖች ውስጥ በሚገኙት የአለፋ ወረዳ፣የሰሜን አቸፈር፣የደቡብ አቸፈር እና የጃዊ ወረዳዎች ለበርካታ ዓመታት የተሟላ የመሰረተ-ልማት ተጠቃሚ ያልሆኑ አካባቢዎች ሲሆኑ ነገር ግን ምርታማ አካባቢዎች ናቸው ተብሏል፡፡ ለወትሮውም ብዙ የመሰረተ ልማት ችግር ያለበት ይህ አካባቢ ከዛሬ አምስት ወር በፊት ጀምሮ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ በመቋረጡ የውኃ፣የስልክ፣የጤና አገልግሎቶችን ማግኘት ከባድ ፈተና ሆኖባቸዋል። ለችግሩ መፍትሔ እንዲሰጠው በሚል የአካባቢው ማሕበረሰብ በተደጋጋሚ ለክልሉ የሥራ ኃላፊዎች ጥያቄውን ያቀረበ ቢሆንም ችግሩ ከፍ ያለና የፌደራል መንግስቱ ሥልጣን ነው በሚል መፍትሔ ሊያገኝ አልቻለም፡፡ የሚመለከተው አካል ምላሽ ይሰጠን በማለት በወረዳው ዋና ከተማ ሊበንና ቁንዝላ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞና ሰልፍ እንዲሁም የመንገድ መዝጋት ትግል ማህበረሰቡ ጀምሯል። ከትናንት በፊት በነበረው ተቃውሞ ፖሊስ በወጣቶችና በህዝቡ ላይ በወሰደው እርምጃ 3 ሰዎች ላይ ጉዳት ሲደርስ በ16 ታዳጊ ህፃን ደግሞ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል። የአማራ ክልል መንግስት ጥያቄያችንን በጥሞና አዳምጦ ለጠየቅነው ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጠን ሲሉ አሳስበዋል ሲል አሻራ ሚዲያ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply