
አሳዛኝ ዜና! በሰበታ ቤታቸው የፈረሰባቸው ባልና ሚስትን ጨምሮ በአራት ሰዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሶስቱ ተገደሉ፤ አንደኛው ቆስሎ መትረፉ ተሰምቷል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)… ግንቦት 5/2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በሰበታ ቤታቸው የፈረሰባቸው ባልና ሚስትን ጨምሮ በአራት ሰዎች ላይ ትላንት ግንቦት 4/2015 ማታ በተከፈተ ተኩስ በተፈጸመ ጥቃት ሶስቱ ተገደሉ፤ አንደኛው ቆስሎ መትረፉን የአሚማ ምንጭ ተናግረዋል። የባል እና ሚስቱ ስርዓተ ቀብር በጉራጌ የሚፈጸም ሲሆን የጎረቤቷ ለቢባ ጀማል ግን በሰበታ መፈጸሙ ተገልጧል። እማት ጉራጌ ሚዲያ ምንጮችን ዋቢ አድርጎ እንደዘገበው ሰበታ ከተማ በኬንተሪ ደረቶ በሚባል ቦታ የአቶ መሀመድና የጎረቤቶቹ ቤቶች የፈረሱት ከትላንት በስቲያ ግንቦት 3/2015 ነበር፤ ሙሉ ሰፈሩ ፈርሶ አልቋል ማለትም ይቻላል። አቶ መሀመድም እዛ ሰፈር ከገባ ወደ 18 አመት ሆኖታል። ቤት ከፈረሰባቸው ሰዎች መካከል የአቶ መሀመድ አብደላን ጨምሮ የሁለት ቤተሰብ አባላት ቤታቸዉ ከፈረሰባቸዉ በኋላ የሚሄዱበት አጥተው ተቸግረዋል። ግንቦት 4/2015 ከሰዓትም አብዛኛው እቃቸውን ወደ ገጠር ከጫኑ በኋላ ሰፈራቸዉ በሚገኝ አንድ ፊኒሽንጉ ያላለቀ የሪል ስቴት ፎቅ ግራውንዱ ላይ ቦታ ያለ በመሆኑ በባለቤቱ መልካም ፍቃድ “ቤት እስክታገኙ እዛ ግቡ” ብሎዋቸዉ ገቡ። ማታ ፖሊሶች መጥተው እነ መሀመድ የተኙበትን የህንፃውን ግራውንድ በር መደብደብ ጀመሩ። መሀመድም ማንነታቸውን ለማጣራት በመጠየቅ ላይ እያለ በሩ በሀይል ተሰበረ፤ በመቀጠልም አቶ መሀመድ አብደላ እንዲሁም ባለቤቱ ለቢባ ጀማል በጥይት ተመተው ሕይወታቸው አልፏል። ጩኸቱን ሰምታ ከመጡት ጎረቤቶች መሀል አራስ የሆነችው ሉባባ ብላቱ በጥይት ተመታ ስትሞት ባለቤቷ ደግሞ ከቆሰለ በኋላ አምልጧል። በጻውሎስ ሆስፒታል ያደረውን አስክሬን አሁን ተቀብለናል። ተስፋ ነዳ – ከጳውሎስ ሆስፒታል። Emat Gurage Media
Source: Link to the Post