
#አሳዛኝ ዜና በሰ/ሜንና ደ/አቸፈር ወረዳዎች ውሀና መብራት ይሰጠን ብለው ተቃውሞ ባሰሙ ወጣቶች ላይ ፖሊስ በተኮሰው ጥይት በወጣቶች እና ህፃናት ላይ የአካል ጉዳትና የህይወት እልፈት እንዲፈጠር ማድረጉ ተሰማ! መጋቢት 04 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ የወረዳው ፖሊስ በወጣቶች ላይ በከፈተው ተኩስ ሶስት ወጣቶች መመታታቸውን ለአሻራ የደረሱ ምንጮች ገልጸዋል። በዚህም የ16 አመት ልጅ የሆነው ወጣት ኤርሚያስ አብየ በጥይት ተመቶ በጥበበ ጊወን ሆስፒታል ኮማ ውስጥ ቆይቶ ዛሬ መሞቱ ታውቋል። በማዕከላዊ ጎንደር፣በምዕ/ጎጃም እና በአዊ ዞኖች ውስጥ በሚገኙት የአለፋ ወረዳ፣የሰሜን አቸፈር፣የደቡብ አቸፈር እና የጃዊ ወረዳዎች ለበርካታ ዓመታት የተሟላ የመሰረተ-ልማት ተጠቃሚ ያልሆኑ አካባቢዎች ሲሆኑ ነገር ግን ምርታማ አካባቢዎች ናቸው፡፡ ለወትሮውም ብዙ የመሰረተ ልማት ችግር ያለበት ይህ አካባቢ ከዛሬ አምስት ወር በፊት ጀምሮ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ተቋርጧል። ከዚህ ጋር በተያያዘ የውኃ፣የስልክ፣የጤና አገልግሎቶችን ማግኘት ከባድ ፈተና ሆኖባቸዋል። ለችግሩ መፍትሔ እንዲሰጠው በሚል የአካባቢው ማሕበረሰብ በተደጋጋሚ ለክልሉ የሥራ ኃላፊዎች ጥያቄውን ያቀረበ ቢሆንም ችግሩ ከፍ ያለና የፌደራል መንግስቱ ሥልጣን ነው በሚል መፍትሔ ሊያገኝ አልቻለም፡፡ የሚመለከተው አካል ምላሽ ይሰጠን በማለት በወረዳው ዋና ከተማ ሊበንና ቁንዝላ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞና ሰልፍ እንዲሁም የመንገድ መዝጋት ትግል ማህበረሰቡ ጀምሯል። በትናንት በፊት በነበረው ተቃውሞ ፖሊስ በወጣቶችና በህዝቡ ላይ በወሰደው እርምጃ 3 ሰዎች ላይ ጉዳት ሲደርስ በ16 ታዳጊ ህፃን ደግሞ ህይወቱ ሊያልፍ ችሏል። የአማራ ክልል መንግስት ጥያቂያችንን በጥሞና አዳምጦ ለጠየቅነው ጥያቄ ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጠን ሲሉ አሳስበዋል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post