አሳዛኝ ዜና! በሸዋሮቢት ከተማ ለወለጋ ሰማዕታት ድምጽ በመሆናቸው የታሰሩ የሸዋሮቢት ድምጾች ይፈቱ በሚል ሲጠይቁ በነበሩ ወገኖች ላይ የጸጥታ አካላት በከፈቱት ተኩስ እስካሁን በደረሰን መረጃ…

አሳዛኝ ዜና! በሸዋሮቢት ከተማ ለወለጋ ሰማዕታት ድምጽ በመሆናቸው የታሰሩ የሸዋሮቢት ድምጾች ይፈቱ በሚል ሲጠይቁ በነበሩ ወገኖች ላይ የጸጥታ አካላት በከፈቱት ተኩስ እስካሁን በደረሰን መረጃ ሁለት ሰልፈኞች ተገድለዋል፤ በርካቶች መቁሰላቸውም ተሰምቷል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሰኔ 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ሰኔ 24/2014 በግፍ የታሰሩ ሁለቱ የወለጋ ሰማዕታት ድምጾች እንዲፈቱ ሲጠይቁ በዋሉ ነዋሪዎች ላይ ከምሽቱ 1:30 ላይ ተኩስ በመክፈት በሁለት ሰልፈኞች ላይ ግድያ መፈጸማቸው እና በርካቶችን ማቁሰላቸውን የአሚማ ምንጮች ከስፍራው ገልጸዋል። አሚማ ቃለ መጠይቅ እያደረገ ሳለም የጥይት ድምጽ በየአቅጣጫው ይሰማ እንደነበር አረጋግጧል። አካባቢው ወደ ሰላም እንዲመጣ ለአፈና የተላኩ አካላትም ሆነ ላኪዎች በአስቸኳይ ወደ ቀልባቸው በመመለስ ግድያቸውንና አፈናቸውን እንዲያቆሙ፤ የአፈኗቸውንም እንዲፈቱ ከከተማው ህዝብ ጥሪ እየቀረበ ነው። በይፋት ቀጠና የመንግስት አካላት ድጋፍ ያለው አሸባሪው ኦነግ ሸኔ የሚሰለጥንባቸው አካባቢዎች በግልጽ እየታወቀ እርምጃ ለመውሰድ ያልደፈረ መንግስት በንጹሃን ሰልፈኞች ላይ በመተኮስ ደም ማፍሰስን መምረጡ እንዳሳዘናቸውም ነዋሪዎች ገልጸዋል። የሽብር ቡድኑ በአካባቢው ባሉ የጸጥታ አካላት እና በነዋሪዎች ላይም ከኦሮሚያ ልዩ ዞን እየተሽከረከረ በመምጣት በተደጋጋሚ ግድያ እየፈጸመ መሆኑ ይታወቃል። የሽብር ቡድኑ አባላት ከኦሮሚያ ልዩ ዞን እየተንቀሳቀሱ ከፈጸሟቸው ግድያዎች መካከል እንደአብነት ለማስታዎስ:_ (1) ግንቦት 10/2014 አመሻሹን በኤፍራታ ግድም ወረዳ ጀብውሃ ባሉ የአማራ ልዩ ኃይል አባላት ላይ በከፈተው ጥቃት አንድ ልዩ ኃይል ቆስሏል። ግንቦት 11/2014 በፓትሮል ይዘው ለህክምና እርዳታ ወደ ሸዋሮቢት እየተጓዙ ሳሉ በደፈጣ በተፈጸመ ተጨማሪ ጥቃት 3 የልዩ ኃይል አባላት መገደላቸው ይታወሳል። (2) ግንቦት 27/2014 ከጠዋቱ 2:15 ላይ በከሚሴ ዞን አርጡማ ፉርጢ ወረዳ የመሸገው አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ወደ የለን በሞተር እየተጓዙ በነበሩ በሁለት የአማራ አርሶ አደሮች ላይ በኤፍራታ ግድም ወረዳ ካራቆሪ ላይ የደፈጣ ግድያ ፈጽሟል። የሽብር ቡድኑ በእለቱም:_ 1) ተፈራ አውግቸው እና 2) ሁሴን ቢያድጎ የተባሉ የአማራ አርሶ አደሮችን ነው የገደለው። (3) ሰኔ 22/2014 በባቲ አንድ ልዩ ኃይል፣ አንድ ፖሊስ እና አንድ ሚሊሻ ገድለው ተሰውረዋል ተብሏል። (4) ሚያዝያ 9 ቀን 2014 ዓ.ም ከዚህ ባለፈ ይህ ወራሪ እና አሸባሪ ቡድን ባደረገው መስፋፋት በሸዋ ሮቢት እና አካባቢው ጀጀባ ላይ በመሆን ወደ ዙጢና ሸዋ ሮቢት ከተማ ከባድ መሣሪያ በመተኮስ የንጹሃን አማራዎችን ሕይወት መቅጠፉ እና የሞላሌ ቀበሌን ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ማውደሙ አይዘነጋም። እንዲህ ዓይነት የተደራጀ የስጋት ቀጠና በሆነው የይፋት አካባቢ አገዛዙ በህዝቡ ላይ እያሳየ ያለው የአፈና አካሄድ ብዙዎችን በእጅጉ እያሰሰበ ነው። እባክዎትን ይህን ሊንክ በማጋራት ተኩስ ለተከፈተበት ወገኖ ድምፅ ይሁኑ:_ https://youtu.be/f5Rbrl2DPY0

Source: Link to the Post

Leave a Reply