You are currently viewing አሳዛኝ ዜና! በሻሸመኔ ከተማ የሟቾች ቁጥር 37 መድረሱ ተሰማ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ …    የካቲት 2 ቀን 2015 ዓ/ም          አዲስ አበባ ሸዋ ተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል በሰ…

አሳዛኝ ዜና! በሻሸመኔ ከተማ የሟቾች ቁጥር 37 መድረሱ ተሰማ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … የካቲት 2 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል በሰ…

አሳዛኝ ዜና! በሻሸመኔ ከተማ የሟቾች ቁጥር 37 መድረሱ ተሰማ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … የካቲት 2 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል በሰበሰበው መረጃ መሠረት የተገደሉት የሰማዕታት ቁጥር 37 መድረሱን ዘግቧል። ከሰማዕታቱም መካከል ጥር 30/2015 ያረፉትና በዕለቱ በሻሸመኔ ደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቅዳሴን ያደረሱት ቀሲስ ሐረገ ወይን ይገኙበታል። በሻሸመኔ ከተማ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በተደረገ የተቀናጀ ጥቃት ሕይወታቸው ያለፈ የሰማዕታት አስክሬን ትናንት ምሽት 4:30 ከደብረ ስብሐት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በመኪና ተጭኖ እንደወጣ የዐይን ዕማኞች የገለጹ ሲሆን ሕገ ወጡ ቡድንም ፎቶ ለመነሳት የሰማዕታት አስክሬን እስኪነሳ እንኳን አለመጠበቁ የጭካኔያቸውን ጥግ የሚያሳይ ነው ሲሉ ገልፀዋል። በሻሸመኔ መልካ ኦዳ ሆስፒታል የገቡ ተገቢውን ሕክምና እንዳያገኙ መከልከላቸውና ወደ ሌላ ሆስፒታል ሪፈር የተጻፈላቸውም እንዳይወጡ መደረጉ ነው። አለፍ ሲልም መረጃቸውን በማቃጠል ቤተሰብ እንዳያገኛቸው መደረጉና የተጎዱትም ምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳሉ የማይታወቅ ሲሆን ቤተሰቦቻቸውም ጭምር ወደ ሆስፒታሉ እንዳይገቡ ተከልከለዋል። ያረፉትም አስክሬን ለቤተሰቦቻቸው እንዳይሰጥም ክልከላ መደረጉ ተገልጿል። ሆስፒታሉም በኦሮሚያ ልዩ ኃይል ተከብቦ እየተጠበቀ ነው። ምንም እንኳን የተገደሉ ኦርቶክሳውያን ቁጥር እንዳይታወቅ የመረጃ ማጥፋት ቢሰራም በደረሰን መረጃ የሟቾች ቁጥር ከ37 በላይ መድረሱን ምንጮች ጠቁመዋል ሲል ተሚማ ዘግቧል። በተጨማሪም መጪው የካቲት 5 በቅዱስ ሲኖዶስ በሚመራው ዓለም አቀፍ ሰላማዊ ሰልፍ የሻሸመኔ ሕዝበ ክርስቲያን እንዳይሳተፍ ወጣቶችን ቤት ለቤት እየሄዱ ማስፈራራትና ድብደባ እየተፈጸመ እንደሚገኝም ገልጿል። ምንጭ :- ተዋህዶ ሚዲያ ማዕከል

Source: Link to the Post

Leave a Reply