አሳዛኝ ዜና! በሽብር ተግባር የተሰማሩት የጉምዝ ታጣቂዎች ከወንበራ ወረዳ ዶቢ ተነስቶ ወደ ቻግኒ በሚጓዝ በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በተሳፈሩ ንፁሀን ላይ በፈፀሙት አሰቃቂ ጭፍጨፋ ከ55 በ…

አሳዛኝ ዜና! በሽብር ተግባር የተሰማሩት የጉምዝ ታጣቂዎች ከወንበራ ወረዳ ዶቢ ተነስቶ ወደ ቻግኒ በሚጓዝ በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በተሳፈሩ ንፁሀን ላይ በፈፀሙት አሰቃቂ ጭፍጨፋ ከ55 በ…

አሳዛኝ ዜና! በሽብር ተግባር የተሰማሩት የጉምዝ ታጣቂዎች ከወንበራ ወረዳ ዶቢ ተነስቶ ወደ ቻግኒ በሚጓዝ በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ በተሳፈሩ ንፁሀን ላይ በፈፀሙት አሰቃቂ ጭፍጨፋ ከ55 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የዐይን እማኞች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ህዳር 5 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በሽብር ተግባር የተሰማሩት የጉምዝ ታጣቂዎች ህዳር 4ለ5 ቀን 2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 11 ሰዓት አካባቢ ተነስቶ ከወንበራ ወረዳ ዶቢ ተነስቶ ድባጤን አቋርጦ ወደ ቻግኒ እያቀና በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ተሳፍረው በነበሩ ንፁሀን ዜጎች ላይ ቂዶህ በተባለ ስፍራ አሰቃቂ ጭፍጨፋ ፈፅመዋል። ከወንበራ ወረዳ ዶቢ ተነስቶ ወደ ቻግኒ ድባጤን አቋርጦ ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ባስ ላይ የጉምዝ ታጣቂዎች በፈፀሙት አሰቃቂ ጥቃት ከ55 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የዐይን እማኞች ተናግረዋል። በተፈፀመው ዘግናኝ ጥቃት ከተገደሉት ከ55 በላይ ከሚሆኑት ሰዎች መካከልም አብዛኞቹ አማራዎች መሆናቸውን ነው ነዋሪዎች የገለፁት። በመኪና ላይ እያሉ ከተገደሉት መካከል ሻለቃ አበራ ረጋሳ፣ሀይሉ ረጋሳ እና ነመራ ረጋሳ የተባሉ 3 ወንድማማቾች እንደሚገኙበት የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ከባሩዳ ወደ ቻግኒ በሚሄድ የህዝብ ማመላለሻ መኪና ላይም ተመሳሳይ ጥቃት መፈፀሙንና ብዙ ጉዳት አለመድረሱን ነው ምንጮች የተናገሩት። ለጊዜው የተጎዳው የሰው ሀይል ምን ያህል እንደሆነ ነዋሪዎች ባያውቁም በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ በጉምዝ ታጣቂዎች ጥቃት ከተፈፀመባቸው ቀበሌዎች መካከል ያምፕ፣ውብሊሽና ቂዶህ ይገኙበታል። በተጨማሪ ጋሌሳ፣ኮመድ ባዚ፣ሳሰማንደንና አግወቶክ ቀበሌዎች የስጋት ቀጠና መሆናቸውን በመጠቆም ጥንቃቄ እንዲደረግ ሲሉ ነዋሪዎች አሳስበዋል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል ቆስለዋል የተባሉትን የድባጤ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ደበሌ በልጋፎን አነጋግሯል። አቶ ደበሌም ትናንት ህዳር 4 ቀን 2013 ዓ.ም ያምፕ በተባለ አካባቢ የቆሰሉ የፀጥታ አካላትን ወደ ድባጤ ለማምጣት በሚል ህዳር 4ለ5 ንጋት 11 ሰዓት አካባቢ ወደ ያምፕ እየተጓዝን ባለንበት ወቅት መንገድ ላይ ጠብቀው የቆዩ የጉምዝ ታጣቂዎች/ሽፍቶች መኪና ላይ ሳለን ተኩስ በመክፈት ጉዳት አድርሰዋል ብለዋል። በመከላከያ ኦራል እየተጓዝን ሳለን ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት አቶ ደበሌ እጃቸው ላይ መጠነኛ ጉዳት እንደደረሰባቸው ገልፀው በተጨማሪም ከመከላከያ ሰራዊት 2 እና ከቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል 2 የልዩ ሀይል አባላት መቁሰላቸውንና ከጠላት ደግሞ በተሰጠው የአፀፋ መልስ 3 ታጣቂዎች ስለመገደላቸው ተናግረዋል። በትናንትናው እለት ከቀኑ 11 ሰዓት አካባቢ ያምፕ በተባለ ቀበሌ የጉምዝ ታጣቂዎች በፖሊስ አባላት ላይ ድንገት በፈፀሙት ጥቃት 2 የፖሊስ አባላት፣ አንድ ሲቪል የቆሰሉ ስለመሆናቸውና ሌላ አንድ ሲቪል ደግሞ በተፈፀመበት ጥቃት ስለመገደሉ አስታውቀዋል። ጥቃቱን የፈፀሙት በመተከል የተለያዩ አካባቢዎች እየተንቀሳቀሱ በህዝብ ላይ ጉዳት ሲያደርሱ የነበሩ የጉምዝ ታጣቂዎች ስለመሆናቸው ተገልጧል። በድባጤ ወረዳ ውብሽ በተባለ ቀበሌም አስማማው የተባለ የግብርና ባለሙያ በእለተ ሀሙስ ህዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም በስራ ላይ እያለ በሽብር ተግባር በተሰማሩ ታጣቂዎች በተተኮሰበት ጥይት ተገድሏል ብለዋል። በህዝብ ባስ ላይ ጥቃት ስለመፈፀሙ መስማታቸውን ከማረጋገጥ ያለፈ ምን ያህል ሰዎች እንደተገደሉ መረጃውን እንዳልደረሳቸው ነው አቶ ደበሌ ያስታወቁት። ያምፕ ቀበሌ ላይ ከቆሰሉት የፖሊስ አባላት መካከል ም/ሳጅን አበበን በስልክ ያነጋገርን ሲሆን አባሉም ግራ ታፋውን እንደተመታ ገልጧል፤ ኢንስፔክተር አበራ የተባለ አመራር፣ አንድ ገበሬ መቁሰለላቸውንና አንድ ሲቪል ተገድሎ ስለመገኘቱ አስታውቋል። ከአካባቢው ነዋሪዎች እና ከድባጤ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ከአቶ ደበሌ በልጋፎ ጋር ያደረግነውን ቆይታ በአማራ ሚዲያ ማዕከል የምናጋራ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply