አሳዛኝ ዜና! በአርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ ሁሩታ ዶሮ ቀበሌ በአማራ ላይ የሚፈጸመው አሳዛኝ ጥቃት እንደቀጠለ ነው፤ የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን በፈጸመው ጥቃት አንዲት እናት ከእነ 6 ወር ህጻን…

አሳዛኝ ዜና! በአርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ ሁሩታ ዶሮ ቀበሌ በአማራ ላይ የሚፈጸመው አሳዛኝ ጥቃት እንደቀጠለ ነው፤ የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን በፈጸመው ጥቃት አንዲት እናት ከእነ 6 ወር ህጻን ልጇ ጨምሮ 9 አማራዎች በግፍ ተገድለዋል። ጥቅምት 27 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ ባህርዳር በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ በአማራ ተወላጆች ላይ አሰቃቂ ግድያ በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ስለመሆኑ በተለያዩ ጊዜያት የሚወጡ መረጃዎች እያመለከቱ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ከስፍራው ለማጣራት እንደሞከረው አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ጥቅምት 26/2015 ዓ/ም ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ አሸባሪው እና ወራሪው የኦነግ ሸኔ ቡድን በአርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ ሁሩታ ዶሮ ቀበሌ በመንበረ ሕይወት የገጠር ከተማ 9 አማራዎችን በአሰቃቂ መልኩ ገድሏል። ከመኖሪያ ቤታቸው በግፍ የተገደሉትም ሰላም የተባለች እናት ከእነ 6 ወር ህጻን ልጇ፣ አንዲት የነርስ ባለቤት እና 7 ወንዶች በድምሩ 9 አማራዎች ማንነታቸው እንደ ወንጀል ተቆጥሮ በጥይት እና በስለት ተጨፍጭፈው ተገድለዋል፤ በደረሰባቸው ጥቃት ቆስለው ወደ አዳማ ሆስፒታል የተወሰዱ እንዳሉም ተነግሯል። በአርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ ሁሩታ ዶሮ ቀበሌ ከናዝሬት በቅርብ ርቀት አዲስ ህይወት ላይ:_ 1) ጥቅምት 20/2015፣ አንድ፣ 2) ጥቅምት 23/2015፣ አምስት በድምሩ ስድስት አማራዎች (ሁለት ወጣቶች (ወንድ እና ሴት)፣ 4 አባቶች) በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ በግፍ መገደላቸውን አሚማ መዘገቡ ይታወሳል። ከተገደሉት 6 ንጹሃን በተጨማሪ ሌሎች 6 አማራዎችም በያዝነው የጥቅምት ወር አጋማሽ አካባቢ መገደላቸውን የነገሩን ከአካባቢው የሸሹ ምንጮች በዚህ ወር ብቻ አዲስ ህይወት ላይ 12 አማራዎች በማንነታቸው ምክንያት በአሰቃቂ መልኩ ተገድለዋል። 3) ከአዲስ ህይወት በ1 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኘው በመንበረ ህይወት የገጠር ከተማም ጥቅምት 26/2015 ከምሽቱ 2 ሰዓት ጀምሮ የሽብር ቡድኑ አባላት ሌሊቱን በፈጸሙት ጥቃት 9 አማራዎች ተገድለዋል። በሁለቱ መንደሮች በያዝነው የጥቅምት ወር ብቻ በድምሩ 21 አማራዎች ተጨፍጭፈል። መንግስት እንዲደርስለት በተደጋጋሚ እየጠየቀ ቢሆንም ሰሚ ያጣው በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች የሚገኘው አማራ ቀድሞ ጊዜውን በዋጀ መልኩ ራሱን ባለመደራጀቱ እና የሚደርስለት በማጣቱ በጥላቻ እና በሀሰት ትርክት ባበዱ የታጠቁ የእሳቤ ድሃዎች በየጊዜው አሳዛኝ በሆነ መልኩ ለዘመናት ከሚኖርበት ቀዬው እየተፈናቀለ፣ እየተሳደደ እና እየተጨፈጨፈ ይገኛል። ዘገባው የአሚማ ነው ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply