You are currently viewing አሳዛኝ ዜና! በጊዳ አያና ከተማ ቆይተው ወደ አንዶዴ ዲቾ በመኪና ሲጓዙ በዘረኛውና አራጁ ኦነግ ሸኔ የታገቱትን ወገኖች በ400 ሽህ ብር ለማስለቀቅ ወደ ጫካ ያቀኑ 3 ሰዎች አለመመለሳቸው ተ…

አሳዛኝ ዜና! በጊዳ አያና ከተማ ቆይተው ወደ አንዶዴ ዲቾ በመኪና ሲጓዙ በዘረኛውና አራጁ ኦነግ ሸኔ የታገቱትን ወገኖች በ400 ሽህ ብር ለማስለቀቅ ወደ ጫካ ያቀኑ 3 ሰዎች አለመመለሳቸው ተ…

አሳዛኝ ዜና! በጊዳ አያና ከተማ ቆይተው ወደ አንዶዴ ዲቾ በመኪና ሲጓዙ በዘረኛውና አራጁ ኦነግ ሸኔ የታገቱትን ወገኖች በ400 ሽህ ብር ለማስለቀቅ ወደ ጫካ ያቀኑ 3 ሰዎች አለመመለሳቸው ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… መስከረም 9 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ከተማ ቆይተው ወደ አንዶዴ ዲቾ በመኪና ሲጓዙ በዘረኛውና አራጁ ኦነግ ሸኔ ተመርጠው መስከረም 6 ቀን 2014 የታገቱት 2 አማራዎች 4ኛ ቀናቸው ተቆጥሯል። በ200 ሽህ ብር ከከፈላችሁ እለቃቸዋለሁ በማለት አሳስሯቸዋል፣ ከታጋቾች ጋር ጠብም አለበት ለተባለ ለአንዶዴ ዲቾ ነዋሪ እንዲያስረክቡ አዞ ነበር። ይሁን እንጅ የተጠቆመው ሰው ገንዘቡን ለመቀበል ፍቃደኛ ባለመሆኑ የገንዘቡን መጠን ከ200 ሽህ ወደ 400 ሽህ ብር በማሳደግ ጫካ ድረስ ይዘው ከመጡ እንደሚለቅላቸው በመግለፁና ታጋቾችም ለገንዘብ ብላችሁ ከምንሞት እባካችሁ እያስባለ በማሰቃየቱ የተባለውን ብር ይዘው 3 ሰዎች ወደ ጫካ እንዲሄዱ ተደርጓል። መስከረም 7 ቀን 2014 አራት መቶ ሽህ ብር ይዘው ወደ ጫካ የገቡት 3ቱ አማራዎችም እስከዛሬ ድረስ አለመመለሳቸውን አሚማ አረጋግጧል። ገንዘቡን ወስደው እንዳስረከቡ የተናገሩት ቤተሰቦችም አሁን ላይ ስልካቸው ተዘግቷል። በርካታ የአካባቢው ማህበረሰብ ብዙ የቡድኑን የጭካኔ መገለጫዎችን በመጥቀስ ላይለቃቸው ይችላል ሲል ከፊሉ ደግሞ ፈጣሪ ያውቃል ሲል ይማፀናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply