አሳዛኝ ዜና! በጊዳ አያና ወረዳ የኡኬ ቀርሳ አማራዎች ላይ ዳግማዊ የተደራጀ ወረራ እና ከፍተኛ ጥቃት እየተፈጸመ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ህዳር 27…

አሳዛኝ ዜና! በጊዳ አያና ወረዳ የኡኬ ቀርሳ አማራዎች ላይ ዳግማዊ የተደራጀ ወረራ እና ከፍተኛ ጥቃት እየተፈጸመ ነው ሲሉ ነዋሪዎች ተናገሩ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ህዳር 27 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን በጊዳ አያና ወረዳ የኡኬ ቀርሳ አማራዎች ላይ ዳግማዊ የተደራጀ ወረራ እና ከፍተኛ ጥቃት እየተፈጸመባቸው መሆኑን ከጥቃቱ የተረፉ ነዋሪዎች ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተናግረዋል። ህዳር 25/2015 ከነቀምት ወደ ኡኬ ቀርሳ የመጣው ከ25 እስከ 30 መኪና የሚደርስ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል፣ የኦነግ ሸኔ አባላትና ሌሎች የከባቢ የጸጥታ አካላት ህዳር 26/2015 ወደ አንገር ጉትንና አካባቢው መውጣታቸው ታውቋል። ከመውጣታቸው በፊት ግን ህዳር 25/2015 በኡኬ ቀርሳ ከፍተኛ የሆነ ዝግጅት ተደርጎ ከአሸባሪው ኦነግ ሸኔ አባላትና ከወጣቶች ጋር በመሆን አማራዎችን ለማጥቃት ከፍተኛ ምክክር ሲደረግ ስለማደሩ ተገልጧል። ከጭፍጨፋ የተረፉ እና በጫካ መሆናቸውን የገለጹ ምንጮች እንደሚሉት አድርገውታል ከተባለው ምክክር በኋላ በጫካ ያለው የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን ወደ ኡኬ ቀርሳ በመምጣት ዙሪያውን በመክበብ በአማራ ላይ ጭፍጨፋውን፣ቃጠሎ እና ዝርፊያውን እንዲፈጽም ተደርጓል። ከቀኑ 10 ሰዓት የጀመረው ጥቃት የቡድን መሳሪያዎችን ጭምር በመጠቀም በሰላማዊ አማራዎች ላይ ግድያ፣ማፈናቀል እና ማሳደዱ ተፈጽሟል፤ ይፋዊ ጦርነቱም እስከ ምሽቱ 1 ሰዓት ድረስ መቆየቱን ምንጮች ተናግረዋል። በምስራቅ ወለጋ ሳሲጋ ወረዳ ህዳር 25/2015 ከምስራቅ ወለጋ የመጣው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ጦርነቱን የከፈተው የአማራ ሚሊሾችን፣ ሴቶችና ህጻናትን በሳሲጋ ወረዳ በጣሳ ጃርሶ ቀበሌ ሀያ አራት በሚባል አካባቢ ነበር። አማራዎች እየተገደሉ ነው፤ በየጫካው እየተሳደዱ ነው፤ ቤቶች ክፉኛ እየተቃጠሉ ነው እንዲሁም ሰላማዊ ሰዎች በቤታቸው ውስጥ በጥይትና በስለት እየተገደሉ ነው ሲሉ የአሚማ ምንጮች ገልጸዋል። ጳጉሜ 4/2014 ከ50 በላይ አማራዎች በኦነጋዊያን በግፍ የተጨፈጨፉባት ኡኬ ቀርሳ አሁንም ህዳር 26/2015 ከፍተኛ ወረራ ተፈጽሞባት በኦነግ ሸኔ እና በኦሮሚያ ልዩ ኃይል የተያዘች መሆኗን በመግለጽ በአስቸኳይ የድረሱልን ጥሪ ቀርቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply