You are currently viewing አሳዛኝ ዜና! በጊዳ አያና የአንዶዴ ቀበሌ ነዋሪዎች ሕይወታችንን አትርፉ ሲሉ እየተማጸኑ ስለመሆኑ እናት ፓርቲ ገለጸ።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ …   መጋቢት 7 ቀን 2015 ዓ/ም…

አሳዛኝ ዜና! በጊዳ አያና የአንዶዴ ቀበሌ ነዋሪዎች ሕይወታችንን አትርፉ ሲሉ እየተማጸኑ ስለመሆኑ እናት ፓርቲ ገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … መጋቢት 7 ቀን 2015 ዓ/ም…

አሳዛኝ ዜና! በጊዳ አያና የአንዶዴ ቀበሌ ነዋሪዎች ሕይወታችንን አትርፉ ሲሉ እየተማጸኑ ስለመሆኑ እናት ፓርቲ ገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … መጋቢት 7 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ በአንዶዴ ዲቾ ቀበሌ የቀበሌው ነዋሪ የሆኑ የእድሜ ባለጸጋ አርፈው በአካባቢው የነበረው ማህበረሰብ በለቅሶው ቦታ በድንኳን ውስጥ እንደተቀመጠ ተኩስ እንደተከፈተበቸው በአካባቢው ያሉ ምንጮቻችን ገልጸዋል ብሏል እናት ፓርቲ በመልዕክቱ። ተኩስ የተከፈተብን መጋቢት 6/2015 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት አካባቢ ነው ያሉት ምንጮች የተኩሱን ድምጽ ሰምተን ስንወጣ በበርካታ መኪና የተጫነና “የመከላከያ ሠራዊት ዩኒፎርም የለበሰ ታጣቂ ኃይል” የጥይት በረዶ አወረደብን ስለማለታቸው አስታውቋል። መጋቢት 7 በሰላም ጉዳይ ውይይት ለማድረግ አንድ የመከላከያ ኃላፊ ከቀበሌው አመራር ጋር ተነጋግረው ሕዝቡ ስብሰባውን እየተጠባበቀ ባለበት ሰዓት ተኩስ ተከፍቶብናል ሲሉ ገልጸዋል። የአካባቢው ምንጮች እንደሚሉት በተከፈተው ተኩስ በሰው ሕይወት ላይ አደጋ እንዳልደረሰ፤ የአካባቢው ነዋሪ ግን በተከፈተበት ተኩስ ተደናግጦ ጫካ የገባ መሆኑንና “በወዛደርነት” ሥራ የሚተዳደር አንድ ግለሰብ በከፍተኛ ሁኔታ ከተደበደበ በኋላ ወደ ጉትን ከተማ ተወስዷል። በተደጋጋሚ ጊዜ ስንገደል ኖርን አሁንም ስቃያችን አላበቃም በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ነን እንዳንወጣም መንገድ ተዘግቷል ሕይወታችንን ታደጉን ሲሉ የተማጽኖ ድምጻቸውን አሰምተዋል። የአገር መከላካያ ሚኒስቴር አባላቱ የተባለውን ፈጽመው ከሆነ ወይም ሌላ አካል በዚህ ሽፋን ጥቃቱን ፈጽሞ እንደሆነ ጉዳዩን እንዲያጣራና ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ እናት ፓርቲ በነዋሪዎች ስም ጠይቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply