You are currently viewing አሳዛኝ ዜና! በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ አርባያ መገንጠያ አካባቢ መሽጎ የነበረ የአገዛዙ ጦር በምኒልክ ብርጌድ ፋኖ ዋና አዛዥ አንተነህ ድረስ እና በሚመራው ፋኖ ላይ ተኩስ ከፍቷል፤ በ…

አሳዛኝ ዜና! በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ አርባያ መገንጠያ አካባቢ መሽጎ የነበረ የአገዛዙ ጦር በምኒልክ ብርጌድ ፋኖ ዋና አዛዥ አንተነህ ድረስ እና በሚመራው ፋኖ ላይ ተኩስ ከፍቷል፤ በ…

አሳዛኝ ዜና! በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ አርባያ መገንጠያ አካባቢ መሽጎ የነበረ የአገዛዙ ጦር በምኒልክ ብርጌድ ፋኖ ዋና አዛዥ አንተነህ ድረስ እና በሚመራው ፋኖ ላይ ተኩስ ከፍቷል፤ በጥቃቱም የተገደሉ እና የቆሰሉ እንዳሉ ለማወቅ ተችሏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ)… ሰኔ 22/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ በጎንደር ዙሪያ ማክሰኝት ወረዳ አርባያ መገንጠያ አካባቢ መሽጎ የነበረ የአገዛዙ ጦር ከጎንደር ተነስተው የእብናት ፋኖዎችን ለመቀበል እየተጓዙ በነበሩ በምኒልክ ብርጌድ ፋኖ በጎንደር ዋና አዛዥ አንተነህ ድረስ እና በሚመራው ፋኖ ላይ ሰኔ 22/2015 ከቀኑ 10 ሰዓት ከምሮ ተኩስ ከፍተዋል። በጥቃቱም የተገደሉ ሁለት የምኒልክ ብርጌድ ፋኖ በጎንደር አባላት መገደላቸው ተሰምቷል፤ የቆሰሉ እንዳሉም ለማወቅ ተችሏል። ተኩሱ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ እንደቀጠለ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። አሚማ መረጃውን እያጣራ ወደ እናንተ የሚያደርስ ይሆናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply