
አሳዛኝ ዜና! በጎንደር ዙሪያ ወረዳ እና በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የብልጽግና ተሿሚዎች ሰርተውታል በተባለ አሻጥር በፋኖዎች ላይ ለተከፈተው ተኩስ በተሰጠ የአጸፋ ምላሽ 5 የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት ሲገደሉ፤ አንድ የፋኖ አባል ቆስሏል፤ ሰባት ሚሊሾች የተማረኩ እና እጅ የሰጡ መሆኑ ተገልጧል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ሀምሌ 12/2015 ዓ/ም_አዲስ አበባ ኢትዮጵያ የጎንደር ዙሪያ ወረዳ እና የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የብልጽግና ተሿሚዎች ሰርተውታል በተባለ አሻጥር ሀምሌ 12/2015 ከቀኑ 12 ሰዓት ገደማ በፋኖዎች ላይ ለተከፈተው ተኩስ በተሰጠ የአጸፋ ምላሽ 5 የፖሊስ እና የሚሊሻ አባላት ሲገደሉ፤ አንድ የፋኖ አባል ቆስሏል፤ ሰባት ሚሊሾች የተማረኩ እና እጅ የሰጡ መሆኑ ተገልጧል። እጅ ያልሰጡ ሚሊሾችም እንደ አማራ እጣፈንታችን ተመሳሳይ መሆኑን አውቀው ለአማራ ፋኖ በጎንደር ዙሪያ እጅ እንዲሰጡ ጥሪ የቀረበ ሲሆን ችግሩም ሆንተብሎ ከከተማዋ በወጡ ካድሪዎች ሴራ እና ክህደት ስለመፈጸሙ ተመላክቷል። ከተማረኩት መካከል የጎንደር ዙሪያ ወረዳ ም/ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ መሆኑ የተነገረለት አቶ ሻምበል ይገኝበታል ተብሏል። ቁጥራቸው አስር የሚሆኑ ሚሊሾች በአስተዳደር ግቢ ውስጥ እንደሚገኙ የገለጹት ምንጮች ከመካከላቸው አንዳንዶች እየሾሎኩ በመውጣት እጅ እየሰጡ ነው ብለዋል፤ አልፎ አልፎም የጥይት ድምጽ እየተሰማ መሆኑ ተገልጧል። በውስን የዞን እና የወረዳ ካድሪዎች በተለይም በጸጥታ መዋቅር ውስጥ ያሉ አመራሮች የሰሩትን ሸፍጥ ተልዕኮ በሰጧቸው አካላት የተጀመረውን ተኩስ ተከትሎ በተወሰደው ራስን የመከላከል እርምጃ ለተገደሉት እና ለቆሰሉት የጸጥታ አካላት የተሰማቸውን ሀዘን በመግለጽ ህመሙ እና ጉዳቱ የጋራ ነውና አሁንም የጸረ አማራ ሴረኞች የክፉ ስራ ተባባሪ ባለመሆን አማራዊ የአብሮነት ትግላችን ይጠናከር ዘንድ ሁሉም ኃላፊነቱን እንዲወጣ ሲል የአማራ ፋኖ በጎንደር ዙሪያ ጥሪ አቅርቧል።
Source: Link to the Post