You are currently viewing አሳዛኝ ዜና! አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በወረራ በያዛት ኡኬ ቀርሳ የሚኖሩ አማራዎችን ጨፈጨፈ፤ ከ50 በላይ አማራ በሆኑ ሴቶች፣ህጻናትና አቅመ ደካሞች ላይ አሰቃቂ ግድያ ስለመፈጸሙ ከዘር ፍጅት ጥ…

አሳዛኝ ዜና! አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በወረራ በያዛት ኡኬ ቀርሳ የሚኖሩ አማራዎችን ጨፈጨፈ፤ ከ50 በላይ አማራ በሆኑ ሴቶች፣ህጻናትና አቅመ ደካሞች ላይ አሰቃቂ ግድያ ስለመፈጸሙ ከዘር ፍጅት ጥ…

አሳዛኝ ዜና! አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በወረራ በያዛት ኡኬ ቀርሳ የሚኖሩ አማራዎችን ጨፈጨፈ፤ ከ50 በላይ አማራ በሆኑ ሴቶች፣ህጻናትና አቅመ ደካሞች ላይ አሰቃቂ ግድያ ስለመፈጸሙ ከዘር ፍጅት ጥቃቱ የተረፉ ተናግረዋል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ጳጉሜ 5 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጉቶ ጊዳ ወረዳ ኡኬ ቀርሳ የተባለች የገጠር ከተማ በአሸባሪው እና ወራሪው ኦነግ ሸኔ ጳጉሜ 4/2014 ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በቁጥጥር ስር ውላለች። ለኡኬ ቀርሳ አዋሳኝ ከሆነው ከሳሲጋ ወረዳ ተነስተው በአርጆ ጉደቱ በኩል በ6 መኪና ተጭነው ወደ አካባቢው ተጠግተው አድረዋል የተባሉት የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን አባላት እና የዘር ማጥፋት ተባባሪዎቻቸው ጳጉሜ 4/2014 ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በዲሽቃ፣በብሬንና በመሰል ቡድን መሳሪያዎች በመታገዝ ጥቃት መፈጸማቸው ታውቋል። ወደ ኡኬ ቀርሳ በሚገባበት ሰዓትም ቁጥራቸው አነስተኛ ከሆኑት ከኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላትና ሚሊሾች ብዙ ትግል ያልገጠመው የሽብር ቡድኑ ልዩ ኃይሎቹ ምሽጉን ብቻ ሳይሆን የነበራቸውን የቡድን መሳሪያ ጭምር ጥለውላቸው ወደ መንደር 10 የሸሹ ስለመሆኑ ከጥቃቱ የተረፉ የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ምንጮች ተናግረዋል። በኡኬ ቀርሳ ላይ የነበሩ የዐይን እማኝ እንደሚሉት በዘር ተኮር ጭፍጨፋው ከ50 በላይ አማራዎች ተገድለዋል፤ ከ20 በላይ የአማራዎችን አስከሬን በዐይኔ ተመልክቻለሁ ብሏል። አሸባሪዎቹ በኡኬ ቀርሳ ከተማ በአማራዎች ቤት ውስጥ እየገቡ በጥይት እና በስለት ጭምር በአሰቃቂ መልኩ የገደሏቸው ስለመሆኑ ተገልጧል። አሸባሪው ሸኔ ከተማዋን ተቆጣጥሮ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን፣ አዋሽንና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንኮችን በመዝረፍ ሰባብሯል የሚሉት የዐይን እማኞች ከግማሽ ቀን በዘለለው ጭፍጨፋ ፖሊስ ጣቢያ ጭምር መቃጠሉን ተናግረዋል። ከተማዋ በሽብር ቡድኑ እየታመሰች፣ አማራዎች ማንነታቸው እንደ ወንጀል ተቆጥሮ በቡድን መሳሪያ ጭምር እየተጨፈጨፉ ቢሆንም የምስራቅ ወለጋ ዞንና የጊቶ ጉዳ ወረዳ የመስተዳድር አካላት ግን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሊደርሱ አልቻሉም ተብሏል። ዞኑ እና ወረዳው እያስገደለን ነው የሚሉት ከጥቃቱ የተረፉ ነዋሪዎች በመኪና ከ2 ሰዓት በታች ለሚወስድ መንገድ “ኃይል እንልካለን” እያሉ ከማዘናጋት ያለፈ ሊደርሱልን አልቻሉም ብለዋል። ከሰሞኑ ኔት ወርክ ተዘግቶ መሰንበቱን እንደ ከፍተኛ ስጋት የቆጠሩ በሌላ አካባቢ የሚኖሩ ቤተሰቦች፣ በበኩላቸው በምስራቅ ወለጋ ባሉ ወገኖቻችን ላይ ጥቃት ሊፈጸምባቸው ይችላል በሚል የጥንቃቄ መልዕክት ማስተላለፋቸው ይታወሳል። በአሙሩ ወረዳ አጋምሳ ላይ በፈጠራ እና በተቀነባበረ መረጃ ከአማራ ክልል የመጣ ፋኖ በንጹሃን ላይ ጥቃት ፈጽሟል በማለት ኦነግ፣ኦኤምኤን እና ሌሎች አካላት በተደራጀ እና በተናበበ መልኩ ከሰሞኑ የዘር ፍጅት ቅስቀሳ ሲያደርጉ መሰንበታቸውና ጥቃቱን ከመፈጸማቸው በፊት ይህ የተለመደ አካሄዳቸው መሆኑን በመግለጽ አሚማ ጥንቃቄ እንዲደረግ ማሳሰቡም አይዘነጋም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply