You are currently viewing አሳዛኝ ዜና! ከህዳር 9 ቀን ጀምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎች በኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና በወረዳው አስተዳዳሪ ታግተው በሚገኙበት ኪረሞ ከተማ ከፍተኛ ተኩስ ተከፍቷል፤ በካምፕ ያሉ ታጋቾች የ…

አሳዛኝ ዜና! ከህዳር 9 ቀን ጀምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎች በኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና በወረዳው አስተዳዳሪ ታግተው በሚገኙበት ኪረሞ ከተማ ከፍተኛ ተኩስ ተከፍቷል፤ በካምፕ ያሉ ታጋቾች የ…

አሳዛኝ ዜና! ከህዳር 9 ቀን ጀምሮ በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎች በኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና በወረዳው አስተዳዳሪ ታግተው በሚገኙበት ኪረሞ ከተማ ከፍተኛ ተኩስ ተከፍቷል፤ በካምፕ ያሉ ታጋቾች የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ በኪረሞ ወረዳ በወረዳው አስተዳደሪ እና በኦሮሚያ ልዩ ኃይል አባላት ታግተው የሚገኙ በመቶዎች የሚቆጠሩ አማራዎች የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው። የታገቱ እና በከተማው ያሉ አማራዎችን እጨፈጭፋለሁ ብሎ ከመጣው ከተባባሪው የኦነግ ሸኔ ቡድን ጋር እየተባበረ ያለው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በንጹሃን ላይ ከፍተኛ ተኩስ መክፈቱ ተገልጧል።; አማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ያነጋገራቸው ምንጮች እንደሚሉት ስማቸው የተመዘገቡ ከ280 በላይ ንጹሃንን ህጻናት፣ሴቶች፣አዛውንትና ወጣቶች ከህዳር 9/2015 ጀምሮ በአስከፊ እገታ ላይ ይገኛሉ፤ ከፊሎቹ መገደላቸውን እየሰማን ነው ብለዋል። እገታው የተፈጸመው በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ በሆነው በአቶ ፍቃዱ ሁንዴ እና በኦሮሚያ ልዩ ኃይል መሆኑን ምንጮች ለአሚማ ገልጸዋል። ልቀቁልን በሚል የሀገር ሽማግሌዎችና የሀይማኖት አባቶች አስተዳዳሪውን በተደጋጋሚ ቢጠይቁም አቶ ፍቃዱ ፍቃደኛ አልሆኑም፤ በኦነግ እንደሚያስጨርሷቸውም ሲዝቱ ነበር ተብሏል። ህዳር 20/2015 ከጠዋቱ 2 ሰዓት ጀምሮ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት እስከ ቀኑ 7 ሰዓት ድረስ የቆዬ ተኩስ በኪረሞ እና አካባቢው አማራዎች ላይ መከፈቱ ተገልጧል፤ በርካታ አማራዎች ተገድለዋል። ተኩሱ የተከፈተውም በአካባቢው የነበረ የኦነግ ሸኔ ገዳይ ቡድን፣ሚሊሻው፣ ያደራጇቸው ወጣቶች እና በልዩ ኃይሉ አማካኝነት ነው፤ የታገቱ፣ በከተማው እና በዙሪያው ያሉ ንጹሃን አማራዎች እባካችሁ በአስቸኳይ ድረሱልን ሲሉ ጥሪ እያሰሙ ነው። ኪረሞ የገባው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ህዳር 9፣10 እና 11/2015 በበርካታ አማራዎች ላይ ግድያ መፈጸሙ እና ከ52 ሽህ በላይ አማራዎችን ከኪረሞ ወደ ሀሮ አዲስ ዓለም ማፈናቀሉ ይታወሳል። አሚማ ደውሎ በሚያነጋግርበት ወቅት ከባድ የተኩስን ድምጽ እየሰማ ነበር።

Source: Link to the Post

Leave a Reply