You are currently viewing አሳዛኝ ዜና! ከአርጆ ጉደቱ ወደ ነቀምት ሲጓዙ የነበሩ ከቶሌ ጭፍጨፋ የተረፉ አማራዎች በመንግስት አካላት በሚደገፈው በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እገታ ተፈጸመባቸው።  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…..

አሳዛኝ ዜና! ከአርጆ ጉደቱ ወደ ነቀምት ሲጓዙ የነበሩ ከቶሌ ጭፍጨፋ የተረፉ አማራዎች በመንግስት አካላት በሚደገፈው በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እገታ ተፈጸመባቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…..

አሳዛኝ ዜና! ከአርጆ ጉደቱ ወደ ነቀምት ሲጓዙ የነበሩ ከቶሌ ጭፍጨፋ የተረፉ አማራዎች በመንግስት አካላት በሚደገፈው በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እገታ ተፈጸመባቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ሰኔ 28 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ከምስራቅ ወለጋ ዞን ዲጋ ወረዳ አርጆ ጉደቱ ከተማ ተነስተው ወደ ነቀምት በሚኒባስ ሲጓዙ የነበሩ ከቶሌ ጭፍጨፋ የተረፉ አማራዎች በመንግስት አካላት በሚደገፈው በአሸባሪው ኦነግ ሸኔ እገታ የተፈጸመባቸው መሆኑን ከጥቃቱ የተረፉ ተናግረዋል። ዘር ተኮር እገታውን የፈጸሙት ከ10 በላይ የሚሆኑ የታጠቁ የሽብር ቡድኑ አባላት ሲሆኑ 7 አማራዎችን አግተው አስቀርተዋል። ከታገቱት መካከል 5 ሴቶች፣ 1 ወንድ እና ከመካከላቸው 2 ህጻናትን ያዘሉ እንደሚገኙበት ተገልጧል። እገታው የተፈጸመውም በዲጋ ወረዳ መቃ በተባለ ጫካ ሲደርሱ ነው አማራ የሆንክ ውረድ በማለት ነው። በተያያዘ ከመኪናው የነበሩ የ7 እና የ8 ዓመት የሚሆኑ ሴት ልጆች እና አንድ ኦሮምኛ መናገር የሚችሉ አባት መትረፋቸው ታውቋል። ይህ ሁሉ ሲፈጸም የደረሰላቸው አንድም የጸጥታ አካል አነበረም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply