አሳዛኝ ዜና! ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ በተወሰዱ አካባቢዎች የሰባሩ ጊዮርጊስ በዓል ከመንበሩ እንዳይወጣ እና በድምቀት እንዳይከበር ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ጥር 19…

አሳዛኝ ዜና! ከአዲስ አበባ ወደ ኦሮሚያ በተወሰዱ አካባቢዎች የሰባሩ ጊዮርጊስ በዓል ከመንበሩ እንዳይወጣ እና በድምቀት እንዳይከበር ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ጥር 19 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከአዲስ አበባ ተወስዶ ወደ ኦሮሚያ ልዩ ዞን ሸገር ሲቲ ብለው በጠሩት አካባቢ በተጠቃለለው ስፍራ ኤርቱ ሞጆ ላይ ያለው የቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት ከመንበሩ እንዳይወጣ ተከልክሎ መዋሉ ተገልጧል። የቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት (የሰባሩ ጊዮርጊስ) ቤተ ክርስቲያን ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ከወረዳ 15 ተወስዶ ወደ ሸገር ሲቲ በተጠቃለለው ኤርቱ ሞጆ አካባቢ ፣ ከካቶሊክ ዩኒቨርስቲ ጎን እንደሚገኝ ይታወቃል። የአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ምንጭ እንደሚሉት ጥር 17/2015 የቅዱስ ጊዮርጊስ ታቦት ለጥር 18 እንዳይወጣ ተከልክሏል፤ በዚህም ታቦቱ ሳይወጣ ቀርቷል። የተገዛው በሬም ሳይታረድ ስለመቅረቱ ፤ ታቦቱም ባለመውጣቱ በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ የሆነ ሀዘን ስለፈጠሩ ተገልጧል። ለምንድን ነው ታቦት እንዳይወጣ የሚከለከለው ብለው የጠየቁ ሶስት ዲያቆናትም በኤርቱ ሞጆ ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸው ታውቋል። የመስተዳድሩ አካላት ለግጭት ዝግጁ ለመሆናቸው እንደማሳያ ይሆን ዘንድ የሚከተለውን ትንኮሳ አድርገዋል:_ 1) ጥር 17/2015 በአካባቢው የሀጫሉ ሁንዴሳን ፎቶ በባነር በትልቁ በማሰራት አቁመዋል። 2) በተጨማሪም ትልቅ የኦሮሚያን አርማ አሰርተው አዋሳኝ ባሉት አካባቢ ከፍ አድርገው በመስቀል እንዲውለበለብ አድርገዋል ሲሉ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply