You are currently viewing አሳዛኝ ዜና! ከዲጋ፣ አርጆ ጉደቱ በበርካታ መኪና ተጭኖ ወደ ቤንሻንጉል የገባ የቡድን መሳሪያ የታጠቀ በብዙ ሽህ የሚቆጠር በመስፋፋት እና በመውረር የሚታወቀው ኦነጋዊ ጥምር ኃይል በከማሽ ዞ…

አሳዛኝ ዜና! ከዲጋ፣ አርጆ ጉደቱ በበርካታ መኪና ተጭኖ ወደ ቤንሻንጉል የገባ የቡድን መሳሪያ የታጠቀ በብዙ ሽህ የሚቆጠር በመስፋፋት እና በመውረር የሚታወቀው ኦነጋዊ ጥምር ኃይል በከማሽ ዞ…

አሳዛኝ ዜና! ከዲጋ፣ አርጆ ጉደቱ በበርካታ መኪና ተጭኖ ወደ ቤንሻንጉል የገባ የቡድን መሳሪያ የታጠቀ በብዙ ሽህ የሚቆጠር በመስፋፋት እና በመውረር የሚታወቀው ኦነጋዊ ጥምር ኃይል በከማሽ ዞን ሚዥጋ ወረዳ ላይ ጦርነት በመክፈት ሰላማዊ አማራዎችን እየገደለ እና እያፈናቀለ መሆኑን በየጫካ የሚሳደዱ ነዋሪዎች ገለጹ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ታህሳስ 1 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ ከምስራቅ ወለጋ ዞን ዲጋ ወረዳ ከአርጆ ጉደቱ በበርካታ ተሽከርካሪዎች ተጭኖ ዛሬ ታህሳስ 1/2015 ወደ ቤንሻንጉል የገባ የቡድን መሳሪያ የታጠቀ በብዙ ሽህ የሚቆጠር ኦነጋዊ ኃይል እየተስፋፋ እና እየወረረ መሆኑ ተገልጧል። በከማሽ ዞን ሚዥጋ ወረዳ ላይ ከረፋዱ 4 ሰዓት ጀምሮ ጦርነት ከፍቷል። የተደራጀ እና የተቀናጀ ጥቃቱን የከፈተውም በበለው ጅጋንፎይ/በሚዥጋ ወረዳ መንደር 42/ተንካራ በሚባል አማራዎች በሚኖሩበት አካባቢ ነው። እየገደለ እና እያፈናቀለ መሆኑን በየጫካ የሚሳደዱ ነዋሪዎች የገለጹ ሲሆን አሁንም ከአርጆ ጉደቱ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኦሮሚያ ልዩ ኃይል እና የአሸባሪው ሸኔ አባላት ወደ መንደር 42 እየገቡ ነው። ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በከባድ መሳሪያ ጭምር በመታገዝ ንጹሃንን እያጠቁ፣ ወረራውን አጠናክረው እየቀጠሉ መሆኑን የአሚማ ምንጮች ገልጸዋል። በአስቸኳይ የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው። ይህ ወረራ መሆኑን የሚገልጹት ነዋሪዎች መንደር 42ን ብቻ ሳይሆን ወረዳውን ጭምር ለመቆጣጠር አልሞ የመጣ የሚመስል ከፍተኛ ኃይል ስለመሆኑ ጠቁመዋል። በተንካራ/መንደር 42/ አማራዎች መውጫ አጥተው እየተሰቃዩ የከረሙበት አካባቢ ነው። የሚዥጋ ወረዳም ሆነ የከማሼ ዞን ንጹሃንን ለመታደግ እየሰሩ አለመሆኑ ምክር እንዳላቸው ያሳያል ብለዋል ምንጮች።

Source: Link to the Post

Leave a Reply