#አሳዛኝ ዜና የሸዋ ደራ አማራ ማንነት ሰብሳቢ ሀይለ ሚካኤል ዓርዓያ ወንድም ዋሲል አርዓያ በኦነግ ታጣቂዎች መገደሉ ተሰማ ። አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 29/2…

#አሳዛኝ ዜና የሸዋ ደራ አማራ ማንነት ሰብሳቢ ሀይለ ሚካኤል ዓርዓያ ወንድም ዋሲል አርዓያ በኦነግ ታጣቂዎች መገደሉ ተሰማ ። አሻራ ሚዲያ ጥቅምት 29/2013 ዓም ባህር ዳር በትናንትናው ዕለት የሸዋ ደራ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ የሆኑት መምህር ሀይለ ሚካኤል ዓርዓያ ወንድም የሆነው ዋሲል ዓርዓያ የተባለው ግለሰብ በኦነግ ታጣቂዎች መገደሉን የሟች ወንድም እና የሸዋ ደራ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ መምህር ሀይለ ሚካኤል ዓርዓያ ለአሻራ ሚዲያ አረጋግጠዋል፡፡ ሟች ዋሲል ዓርዓያ በትናንትናው ዕለት ቅዳሜ ጥቅምት 28 /2013 ዓ.ም ገደል ውስጥ ሞቶ የተገኘ ሲሆን ብዙ ጊዜ የኦነግ ታጣቂዎች በገዳይነት ላለመፈረጅ ከጥይት ባለፈ በተለያዩ አደጋዎች እየዳረጉ እንደሚገድሏቸው ገልጸውልናል፡፡ በሸዋ ደራ አካባቢ የኦነግ ታጣቂዎች በርካታ ንጹሀን አማራዎችን በማንነታቸው ብቻ እየለዩ እየገደሉ እንደሚገኙ ከአሁን በፊት አሻራ ሚዲያ ከቦታው ድረስ መረጃዎች አጠናቅሮ መዘገቡ ይታወሳል፡፡ ዘጋቢ ፡- ማርሸት ጽሀው

Source: Link to the Post

Leave a Reply