You are currently viewing አሳዛኝ ዜና የአንዶዴ ቀበሌ ነዋሪዎች ሕይወታችንን አትርፉ ሲሉ ተማጸኑ! መጋቢት 07 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ በአንዶዴ ዲቾ ቀበሌ የቀበሌ…

አሳዛኝ ዜና የአንዶዴ ቀበሌ ነዋሪዎች ሕይወታችንን አትርፉ ሲሉ ተማጸኑ! መጋቢት 07 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ በአንዶዴ ዲቾ ቀበሌ የቀበሌ…

አሳዛኝ ዜና የአንዶዴ ቀበሌ ነዋሪዎች ሕይወታችንን አትርፉ ሲሉ ተማጸኑ! መጋቢት 07 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ አያና ወረዳ በአንዶዴ ዲቾ ቀበሌ የቀበሌው ነዋሪ የሆኑ የእድሜ ባለጸጋ አርፈው በአካባቢው የነበረው ማህበረሰብ በለቅሶው ቦታ በድንኳን ውስጥ እንደተቀመጠ ተኩስ እንደተከፈተበቸው በአካባቢው ያሉ ምንጮቻችን ገልጸዋል። ተኩስ የተከፈተብን መጋቢት 6/2015 ዓ.ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት አካባቢ ነው ያሉት ምንጮች የተኩሱን ድምጽ ሰምተን ስንወጣ በበርካታ መኪና የተጫነና “የመከላከያ ሠራዊት ዩኒፎርም የለበሰ ታጣቂ ኃይል” የጥይት በረዶ አወረደብን ብለዋል። መጋቢት 7 በሰላም ጉዳይ ውይይት ለማድረግ አንድ የመከላከያ ኃላፊ ከቀበሌው አመራር ጋር ተነጋግረው ሕዝቡ ስብሰባውን እየተጠባበቀ ባለበት ሰዓት ተኩስ ተከፍቶብናል ሲሉ የገለጹት የአካባቢው ምንጮች በተከፈተው ተኩስ በሰው ሕይወት ላይ አደጋ እንዳልደረሰ፤ የአካባቢው ነዋሪ ግን በተከፈተበት ተኩስ ተደናግጦ ጫካ የገባ መሆኑንና “በወዛደርነት” ሥራ የሚተዳደር አንድ ግለሰብ በከፍተኛ ሁኔታ ከተደበደበ በኋላ ወደ ጉትን ከተማ እንደተወሰደ ገልጸዋል። በተደጋጋሚ ጊዜ ስንገደል ኖርን አሁንም ስቃያችን አላበቃም በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ነን እንዳንወጣም መንገድ ተዘግቷል ሕይወታችንን ታደጉን ሲሉ የተማጽኖ ድምጻቸውን አሰምተዋል። የአገር መከላካያ ሚኒስቴር አባላቱ የተባለውን ፈጽመው ከሆነ ወይም ሌላ አካል በዚህ ሽፋን ጥቃቱን ፈጽሞ እንደሆነ ጉዳዩን እንዲያጣራና ለሕዝብ ይፋ እንዲያደርግ እናት ፓርቲ በነዋሪዎች ስም ይጠይቃል። ፈጣሪ ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ እናት ፓርቲ አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ መጋቢት 7/2015 ዓ.ም “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply