You are currently viewing አሳዛኝ ዜና የኦህዴድ ሠራዊት በከባድ መሳሪያ አንድ የሀይማኖት አባትን ጨምሮ አራት እረኞችን ሲገድል ሦስት ሴቶችን ደግሞ ክፉኛ አቆሰለ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ በ…

አሳዛኝ ዜና የኦህዴድ ሠራዊት በከባድ መሳሪያ አንድ የሀይማኖት አባትን ጨምሮ አራት እረኞችን ሲገድል ሦስት ሴቶችን ደግሞ ክፉኛ አቆሰለ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ በ…

አሳዛኝ ዜና የኦህዴድ ሠራዊት በከባድ መሳሪያ አንድ የሀይማኖት አባትን ጨምሮ አራት እረኞችን ሲገድል ሦስት ሴቶችን ደግሞ ክፉኛ አቆሰለ ግንቦት 10 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ በሰሜን ሸዋ ዞን ቀዎት ወረዳ በራሳ ቀጠና በትናንትናው ዕለት ማለትም ግንቦት 9/2015 ዓ.ም በከባድ መሳሪያ በመታገዝ መጠነ ሰፊ ጥቃት በንፁሃን ላይ ከፍቶ የነበረው በኦህዴድ/ኦነግ የሚመራው መከላከያ ሠራዊት ነው በንፁሃን ላይ ጭፍጨፋ የፈፀመው። የአካባቢው የመረጃ ምንጫችን እንደጠቀሱት በኦህዴድ/ኦነግ የሚመራው መከላከያ ሠራዊት ሆን ብሎ ወደ ንፁሃኑ ቤት ባደረገው የከባድ መሳሪያ ድብደባ ነው 5 ንፁሃንን ገድሎ 3 ሴቶችን ክፋኛ ያቆሰለው ብለዋል። የተከበሩ የሃይማኖት አባት እና የአገር ሽማግሌ የነበሩት 1ኛ) ቀሲስ ደረጀ ንጉሴ እንዲሁም ፣በከብት ጥበቃ ላይ የነበሩ 2ኛ) አይፎክሩ ዘየደ 3ኛ) አግዘው በጋሻው 4ኛ) ባቡ የሽዳኛ እና 5ኛ) ወንደሰን አራጌ በመከላከያ ሠራዊቱ በደረሰባቸው የከበድ መሳሪያ ድብደባ ወዲያውኑ ሕይዎታቸው ማለፉ ታውቋል። ይጠብቋቸው የነበሩ በርካታ ከብቶቻቸውም በግፍ በከባድ መሳሪያው ድብደባ ተገድለዋል። ከላይ ከተጠቀሱት ንፁሃን በተጨማሪ በመኖሪያ ቤታቸው ተቀምጠው የነበሩ ሶስት ሴቶች ክፉኛ መቆሰላቸውን ከስፍራው መረጃው ደርሶናል። ከንፁሃን ሞት በተጨማሪ በበርካታ መኖሪያ ቤቶችና በአርሶ አደሩ ሃብት ንብረት ላይ ከባድ ውድመት መድረሱ ተገልጿል። በንፁሃን ዜጎች ላይ እና በንብረቶቻቸው ላይ በመከላከያ ሠራዊቱ በደረሰው ዘግናኝ ጭፍጨፋና ውድመት ምክንያት የአካባቢው ህዝብ ከፍተኛ ቁጣ ውስጥ መግባቱ ተገልጿል። በአማራ ክልል በ ዐብይ አህመድ በይፋ ጦርነት ከታዎጀ ሶስት ሳምንት አልፎታል። ሼር ይደረግ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ይወቀው! “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply