You are currently viewing አሳዛኝ ዜና! የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በኪረሞ ዛሬም ግድያውን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፤ ህዳር 11/2015 ረፋድ ላይ 2 አማራዎችን በአደባባይ ተኩሶ ገድሏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ……

አሳዛኝ ዜና! የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በኪረሞ ዛሬም ግድያውን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፤ ህዳር 11/2015 ረፋድ ላይ 2 አማራዎችን በአደባባይ ተኩሶ ገድሏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ……

አሳዛኝ ዜና! የኦሮሚያ ልዩ ኃይል በኪረሞ ዛሬም ግድያውን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፤ ህዳር 11/2015 ረፋድ ላይ 2 አማራዎችን በአደባባይ ተኩሶ ገድሏል። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ … ህዳር 11 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ እነ አቶ ሽመልስ አብዲሳ ያሰማሩት የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ህዳር 10/2015 በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪረሞ ከተማ ከ8 በላይ አማራዎችን በካምፕ እና በአአባባይ በጥይት ተኩሶ መግደሉ ይታወቃል። ህዳር 9/2015 እና ህዳር 10/2015 ከጊዳ አያና ወደ ኪረሞ የገባው በሽህ የመከቆጠር ልዩ ኃይል በርካታ ሰላማዊ ማራዎችን መግደሉን ተከትሎ ከ50 ሽህ ያላነሰ አማራ ለቆ ወደ ሀሮ አዲስ ዓለም ገብቶ በከፍተኛ ችግር ላይ ይገኛል። በሽህ የሚቆጠር ልዩ ኃይል ከተማዋ ላይ ቁጭ ብሎ ዘራፊዎች በኃይል የአማራውን ሱቅ፣ቤት እና ሆቴል በር እየሰበሩ በመግባት ከህዳር 10 እስከ 11/2015 ዝርፊያ እየፈጸሙ ይገኛሉ። ይህ ብቻ ሳይሆን ልዩ ኃይሉ ዛሬም ግድያውን አጠናክሮ ቀጥሎበታል፤ ህዳር 11/2015 ረፋድ ላይ:_ 1) መሀመድ ከማል እና 2) አህመድ ኩሜ የሚባሉ 2 አማራዎችን በአደባባይ ተኩሶ ገድሏል፤ ይህ ዜና ሲጠናቀር የተኩስ ድምጽ እየተሰማ ነበር። የሟቾች ቁጥር ሊጨምር ይችላል። የአማራዎች የድረሱልን ጥሪ አሁንም ምላሽ አላገኘም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply