አሳድጋለው ብላ በወሰደችው ህጻን ላይ የሰብሃዊ መብት ጥሰት ፈጽማለች የተባለችው ግለሰብ በእስር ተቀጣች፡፡

በአሪ ዞን ጅንካ ከተማ ከልጆቼ ሳልለይ አሳድጋለው ብላ ባመጣችው ህጻን ላይ የሰብሃዊ መብት ጥሰት ፈጽማለች የተባለችው ግለሰብ በ6 አመት እስር መቀጣቷን የጂንካ ከተማ አስተዳደር ለጣቢያችን አስታውቋል፡፡

የጂንካ ከተማ ፍትህ ጽህፈት ቤት የሴቶችና ህጻናት ዐቃቤ ህግ ወ/ሮ ምስር ዘመድኩን ግለሰቧ ጥቃቱን የፈጸሙተ በ12 አመት ህጻን ላይ ነው ብለዋል፡፡

አሳድጋለው ብላ ያመጣችውን ህጻን ከልጆቿ በመለየት በሌላ ክፍል ውስጥ በማኖር ጭካኔና ግፍ በተሞላበት መልኩ ስታሰቃይ እንደነበር ዐቃቤ ህጓ ተናግረዋል፡፡

ወንጀሉን የፈጸሙት ወ/ሮ ካሰች ሲሳይ የተባሉት ግለሰብ በፍርድ ቤቱ በወንጀል ክስ መዝገብ ጥፋተኝነታቸው ተረጋግጦ የ6 አመት እስራት እንደተላለፈባቸው ለጣቢያችን ገልጸዋል፡፡

ስለሆነም ፍርድ ቤቶች ከመቼው ጊዜ በላይ የልጆችን የሰመብሃዊ መብት ሊያስጠብቁ የሚገባው አሁን ነው ሲሉ የህግ ባለሞያዋ ተናግረዋል፡፡

የሰብሃዊ መብት ጥሰት የሚፈጸምባቸው ህጻናት ፤በማህበረሰቡ ውስጥ ሆነ በፍርድ ቤቶች እራሳቸውን መከላከል የሚችሉበት ምንም አቅም እንደሌላቸው ወ/ሮ ምስር ዘመድኩን አንስተዋል፡፡

አሁን ላይ በሃገራችን በተለያዩ አከባቢዎች በልጆች ላይ የሚፈጸሙ የጉልበት ብዝበዛ፤የወሲብ እና አካለዊ ጥቃቶች እየተበራከቱ ነው ብለዋል፡፡

በተለይ ከጎናቸው ማንም የሌላቸው ህጻናት ችግሩ እጅጉን እንደሚበረታባቸው ተናግረዋል፡፡

ስለሆነም የህግ አካላት ከፍርድ ቤቶች ጋር በጋራ በመሆን ለነዚህ ህጻናት የህግ ከለላ ሊሰጥ እንደሚገባ የጂንካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ዐቃቤ ህግ ወ/ሮ ምስር ዘመድኩን አስገንዝበዋል፡፡

መሳይ ገብረ መድህን
ታህሳስ 16 ቀን 2016 ዓ.ም

Facebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Source: Link to the Post

Leave a Reply