
አስመሳዩ አክቲቪዝም የዘነጋቸው፣ በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ በስርዓቱ አገዛዝ ተፈናቅለው ደብረ ብርሃን ከተማ ያሉ ወገኖቻችን አንገብጋቢ ጉዳይ! መጋቢት 05 ቀን 2015 ዓ.ም አሻራ ሚዲያ ፣ በአማራ ክልል የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር፤ በከተማይቱ ያሉትን ተፈናቃዮች ማስተናገድ ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት ማስታወቁ ይታወሳል ። ከአንድ ወር ወዲህ ወደ ከተማይቱ የሚገቡ አዲስ ተፈናቃዮችን መቀበልም ሆነ ወደ መጠለያ ማስገባት ማቆሙንም የከተማይቱ አስተዳደር ገልጿል። ከአዲስ አበባ 130 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው የደብረ ብርሃን ከተማ፤ ባለፉት ሁለት ዓመታት ከመንፈቅ ባሉት ጊዜያት በኦሮሚያ ክልል ከሚገኙ አራቱም የወለጋ ዞኖች እንዲሁም ከአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን የተፈናቀሉ ነዋሪዎችን ስታስተናግድ ቆይታለች። በአሁኑ ወቅት በከተማይቱ በሚገኙ በስድስት ጊዜያዊ የመጠለያ ጣቢያዎች ውስጥ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቃዮች እንደሚገኙ አሻራ በቦታው ያገኘው መረጃ ያመለክታል። ከምስራቅ ወለጋ ዞን፣ ሲቡ ሲሪ ወረዳ ተፈናቅለው ለአንድ ዓመት ያህል በከተማይቱ ተጠልለው የሚገኙት አቶ አህመድ መሐመድ፤ ባለፉት 45 ቀናት ወደ ደብረ ብርሃን የመጡ ተፈናቃዮች መጠለያ ሳያገኙ መቅረታቸውን በተደጋጋሚ ገልፀዋል። የከተማይቱ ኃላፊዎች “ህዝቡ ሲጨምር አንመዘግብም ብለዋል” ሲሉም ባለፉት 30 ቀናት ካሉበት መጠለያ ጣቢያ ሆነው የታዘቡትን አስረድተዋል። የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር በተፈናቃዮች ብዛት ምክንያት አዲስ ተመዝጋቢዎችን እንደማይቀበል አስታውቋል። ተፈናቃዮች፤ በጥላቻ የገነገነው የተረኛውን የኦሮሚያ ክልል መንግሥት፣ ዘር ለይቶ ክልሌን ለቃችሁ ውጡ እያለ ያፈናቀላቸው፤ ከሞት የተረፉ ንጹሃን ለአሻራ ሚዲያ ተናግረዋል ። ሙሉ መረጃውን ከአሻራ ዩትዩብ ቻናል ይከታተሉ ። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24
Source: Link to the Post