አስተሪዮ ማርያም በመርጡለ ማርያም በድምቀት እንዲከበር ላደረጉ አካላት የምስራቅ ጎጃም ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ምስጋና አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 22 ቀን 2015 ዓ…

አስተሪዮ ማርያም በመርጡለ ማርያም በድምቀት እንዲከበር ላደረጉ አካላት የምስራቅ ጎጃም ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ምስጋና አቀረበ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጥር 22 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የአስተርዮ ማርያም ክብረ በዓል በመርጡለ ማርያም ገዳም በሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ክዋኔዎች ከዚህ በፊት ከነበረው አከባበር በተለየ ድምቀት በድምቀት መከበሩን የምስራቅ ጎጃም ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ገልጿል። የአስተሪዮ በዓል በመርጡለ ማርያም፤ ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የምስራቅ ጎጃም፣ ጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ብፁዕ አቡነ ዮሴፍ የሲዳማ፣ አማሮ፣ ቡርጂና አርሲ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስን ጨምር ፣ የመንግስት የሥራ ኀላፊዎች እና በርካታ እንግዶች በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል። በዓሉ በሰላም እንዲከበር የድርሻቸውን ለተወጡ የጸጥታ አካላት ፣የአካባቢው ወጣቶች፣ የሃይማኖት አባቶች ፣የአካባቢው ነዋሪዎችና በዓሉ በተሳካ መልኩ እንዲከበር አስተዋፅኦ ላደረጉ ሁሉ የምስራቅ ጎጃም ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ምስጋና ማቅረቡን ገልጿል ሲል አሚኮ ነው የዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply