አስቸኳይ መረጃ መተከል (አሻራ ጥር 12፣ 2013 ዓ.ም) በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ዱበን ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ዛሬ አመሻሽ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጉምዝ ታጣቂዎች ሰፍረዋል። ቦታው…

አስቸኳይ መረጃ መተከል (አሻራ ጥር 12፣ 2013 ዓ.ም) በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ዱበን ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ዛሬ አመሻሽ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጉምዝ ታጣቂዎች ሰፍረዋል። ቦታው…

አስቸኳይ መረጃ መተከል (አሻራ ጥር 12፣ 2013 ዓ.ም) በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ ዱበን ተብሎ የሚጠራው አካባቢ ዛሬ አመሻሽ ላይ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጉምዝ ታጣቂዎች ሰፍረዋል። ቦታው ለድባጤ፣ወንበራ እና ያሶ ወረዳ አቅራቢያ እንደሆነም መረጃ ደርሶናል።የመረጃ ምንጫችን እንደነገሩን ከሆነ ቦታው ላይ ወታደራዊ ስልጠና በኦነግ እየተሰጣቸው የነበሩ በርካታ ጉምዞች እንደነበሩ እና ዛሬ ደግሞ በሁለት የጭነት መኪና ሙሉ የጉምዝ ታጣቂ እንደገባም አክለው ገልፀውልናል። የመረጃ ምንጫችን እንዳሉት አማራዎች፣አገዎች እና ሽናሻዎች አካባቢውን ለቀው በመውጣታቸው አካባቢው ወደ ምድረ በዳነት እየተቀየረ ነው ያሉት የመረጃ ምንጫችን አሁን ሰው የቀረው ጋሌሳ ብቻ ነው ።ዛሬ የመጡት ጉምዞችም ጋሌሳ ላይ ያለውን አማራ ለመጨፍጨፍ እንዳሰቡ ሰምተናልም ብለዋል። በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት የጉምዝ ታጣቂዎች አማራ ክልልን ጥሰው በመግባት ሰብል በመሰብሰብ ላይ የነበሩ አርሶ አደሮች ላይ ጥቃት ሰንዝረዋል።በጥቃቱም ሁለት አባት እና ልጅ ሲሞቱ አንድ ሰው ከፍተኛ ጉዳት ደርሶበታል።የአማራ ክልል መንግስት እስካሁን ያለው ነገር የለም።

Source: Link to the Post

Leave a Reply