You are currently viewing #አስቸኳይ ዜና ከዛሬ ምሽት ጀምሮ የኦህዴድ ሠራዊት፣የከተማ ፖሊስ እና ሚሊሻዎች ተቀናጅተው ዕንቅስቃሴ ማድረግ መጀመራቸው ተገለፀ! ግንቦት 08 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ በምዕራ…

#አስቸኳይ ዜና ከዛሬ ምሽት ጀምሮ የኦህዴድ ሠራዊት፣የከተማ ፖሊስ እና ሚሊሻዎች ተቀናጅተው ዕንቅስቃሴ ማድረግ መጀመራቸው ተገለፀ! ግንቦት 08 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ በምዕራ…

#አስቸኳይ ዜና ከዛሬ ምሽት ጀምሮ የኦህዴድ ሠራዊት፣የከተማ ፖሊስ እና ሚሊሻዎች ተቀናጅተው ዕንቅስቃሴ ማድረግ መጀመራቸው ተገለፀ! ግንቦት 08 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ በምዕራብ እና ምስራቅ ጎጃም በሚገኙ የአባይ በረሃ ሸለቆማ አካባቢዎች የመከላከያ ሠራዊት ልብስ የለበሱ ኦነጎች በቅጥረኛ ለሆዳቸው ባደሩ የከተማ ፖሊሶች እና ሚሊሻዎች እየተመሩ ውጊያ ለማድረግ ስምሪት መውሰዳቸውን ከውስጥ የመረጃ ምንጫችን አድርሶናል። “በየወረዳው በጎጃም አካባቢ ባሉ በረሃዎች የሚሰለጥን ፍኖ እና እየተደራጀ ያለ ኃይል አለ” በማለት በፖሊስ እና በሚሊሻ መሪነት መከላከያ ተቀናጅቶ እየገባ መሆኑ ታውቋል። ወንበርማ ወረዳ፣ ቡሬ ዙሪያ ወረዳ፣ ቁጭ ንዑስ ወረዳ፣ ጃቢ ጠናን ወረዳ፣ ደንበጫ ዙሪያ ወረዳ እና ደብረ ኤሊያስ ወረዳዎች በአባይ ሸለቋማ በረሃዎች የኦህዴድ/ኦነግ ብልፅግና ሠራዊት ውጊያ ለማድረግ በቲም፣ በጋንታ፣ በሻምበል እና በሻለቃ ተደራጅቶ እየገባ እንደሆነ ታውቋል። በምስራቅ እና በምዕራብ ጎጃም የሚገኝ ማንኛውም አካል በየአካባቢያችሁ ስምሪት ወስዶ ጥሶ እየገባ ያለው አካል ቤተሰብህን ለመግደል መሆኑን አውቀህ በጥብቅ እንድትዘጋጅ ጥሪ ቀርቧል።መንገዶችን በመዝጋት፣እህል ውሃ አለማቀበል፣መረጃ ለፋኖዎች በማቀበል፣ ወዘት ..በማደረግ እንድትዘጋጁ ጥሪ ቀርቧል። በዚህ ውጊያ ለሚደረሰው ጥፋት ከወዲሁ ተጠያቂዎች የጎጃም አስተዳደሮች እና የፀጥታ አካላት ናቸው ተብሏል። በበረሃ ለሚገኝ ማንኛው የአማራ ኃይል መረጃው እንዲደርሳቸው ይደረግ ተብሏል። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply