#አስቸኳይ #የሰከላ ወረዳ አርሶ አደሮች መሬታችንን ያለአግባብ እንድናጣ ተገደናል የሚል አቤቱታ አቀረቡ! ታሕሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ የሰከላ ወረዳ ገጠር መሬት ጽ/…

#አስቸኳይ #የሰከላ ወረዳ አርሶ አደሮች መሬታችንን ያለአግባብ እንድናጣ ተገደናል የሚል አቤቱታ አቀረቡ! ታሕሳስ 25 ቀን 2015 ዓ.ም… አሻራ ሚዲያ ፣ የሰከላ ወረዳ ገጠር መሬት ጽ/ቤት ለአባይ ሳንግብ ቀበሌ የቤቶች ማህበር ቦታ ለመስጠት በሚል ተገቢ ካሳ እና የሃብት ንብረት ቆጠራ ሳይካሄድ የአርሶ አደር ልጆች የቤት መስሪያ ሳያገኙ የአርሶ አደሩን ተክል አዝመራ በመመንጠር ያለአግባብ መሬታችን ተነጥቀናል ሲሉ ለአሻራ ገለፁ። የአርሶ አደሮችን መሬት ንብረት ሳይሸከፍ የሰከላ ወረዳ የገጠር መሬት አስተዳደር መሪዎች በህገወጥ መንገድ ሰብሎቻችን እና ያልደረሱ እፅዋትን በመጨፍጨፍ የግፍ ግፍ ተፈፅሞብናል የሚል አቤቱት በማቅረብ የሚመለከተው አካል ይወቅልን ብለዋል። አቤቱታውን ያደረሱት የአባይ ሳንግብ የደጅ አዝማች ዘለቀ ደስታ አርሶ አደሮችና የአካባቢው ነዋሪ የሆኑ ማህበረሰቦች ናቸው። አርሶ አደሩ በጅምላ ሃብት ንብረቱ እየወደመበት ነው። ግልፅ ወረራ የተፈፀመበት ብለዋል ለአሻራ ባደረሱት ቅሬታ። “ውድ የአሻራ ሚዲያ ቤተሰቦች የአሻራ ሚዲያ ቻናልን ላይክና ሰብስክራይብ በማድረግ ድጋፋችሁን ታሳዩን ዘንድ በአክብሮት እንጠይቃለን።” ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- // Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw // Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 // ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply