አስደሳች ዜና ጀግናው ቤተ ዐማራ ምሰሶ የሆነው ፋኖ በአንድ ዕዝ ለመምራት ስምምነት መፈፀማቸው ተሰማ!! ነሐሴ 28/2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) የምስራቅ አማራ ፋኖ እና የቤተ ዐማራ ፋኖ በ…

አስደሳች ዜና ጀግናው ቤተ ዐማራ ምሰሶ የሆነው ፋኖ በአንድ ዕዝ ለመምራት ስምምነት መፈፀማቸው ተሰማ!! ነሐሴ 28/2014 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) የምስራቅ አማራ ፋኖ እና የቤተ ዐማራ ፋኖ በአንድ ልብ እና በአንድ መምሪያ ትግላቸውን ሊያካሂዱ መሆኑ ተሰምቷል። የምስራቅ አማራ ፋኖ ዋና አዛዥ እና የቤተ ዐማራ ፋኖ ዋና አዛዥ በስምምነታቸው ጠላትን ለመፋለም በቁርጥ መታገል እንደሚያስፈልግና ለዚህም በጋራ ለመስራት ስምምነታቸውን ለሰራዊቶቻቸው አሳውቀዋል። ፋኖ በዚህ መልኩ እየተዋሃደ ከቀጠለ መጭው ጊዜ በቅርብ ጊዜ ነፃነታችንን እንደምናገኝ አልጠራጠርም። የአማራ ህዝብ የመጨረሻው ምሺግ የሆነው ፋኖ ፀረ አማራዎችንና አስተሳሰባቸውን ለመታገል ግደታ የፋኖ በማዕከላዊነት መመራት ያስፈልጋል። የአማራን ህዝብ ከጥቃት ለመከላከል በዋናነት በማዕከላዊነት መስራትን መላመድ ይኖርብናል። ተበታትነን እየሄድን ያለው ነገር ሁሉ ለዘመናት ችግርን ከመውለድ ባለፈ ያተረፈልን ነገር የለም። ስለዚህ ትግላችን በዋናነት የአንድነት ትግሉ ላይ ሊሆንም ይገባዋል። ወጣቱን በዚህ መልኩ እያጠናከሩ መቀጠል የጠላትን እኩይ ዓላማ ተፈፃሚ እንዳይሆን ያደርጋል። በአበው ብሂል “አንድነት ሃይል ነው” እንደሚባለው ህዝባችን ከመሰል ችግሮች እንዲወጣ ሁሉን አቀፍ ትግልን በማዕከላዊነት ላይ ቆመን መፈፀምን ይጠይቃል። ስለሆነም የምስራቅ አማራ ፋኖና የቤተ ዐማራ ፋኖ ያደረጉት የሁለትዮሺ ግንኙነት እጅግ አስፈላጊ እና የተበታተነውን ሃይል ለአንድ ዓላማ እንዲቆም በማድረጉ ከፍተኛ ማህበራዊ ተነሳሺነትን ይፈጥራል። ስለሆነም ወንድም ዋርካው ምሬ ወዳጆ እና ወንድም ሰለሞን አያሌው እያደረጋችሁት ያለው መሰረታዊ የትግል ምዕራፍ በወጣቱ እና በተዋጊ ሰራዊቱ ላይ የሚፍጥረውን የአንድነት ጥምረት እጅግ አስደሳች በመሆኑ ልትመሰገኑ ይገባል። ይህ ሂደት በሌሎች አካባቢዎች ያለውን አወቃቀርም በቅርብ ጊዜ እንደ ድልድይ ሆኖ ሁሉም የፋኖ መዋቅሮች በአንድ የዕዝ ሰንሰለት ተፈፃሚ እንደሚሆን አልጠራጠርም። ፋኖነት ለጠላት ዕሬት ለወገን ደጀን ሆኖ በትውልድ ዘንድ ይሰርፃል። ፋኖ ያሸንፋል!! © አሸናፊ ገናን ፎቶ ኤርሚያስ አያሌው ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply