አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በመተከል ዞን ከቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ  ድጋፍ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ  ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ…

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በመተከል ዞን ከቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ…

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ በመተከል ዞን ከቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ከአንድ ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 26 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በመተከል ዞን የተለያዩ ወረዳዎች በጽንፈኞች በተፈፀመባቸው ጥቃት ከመኖሪያ ቀዬአቸው ለተፈናቀሉ ዜጎች ግምቱ ከአንድ ሚሊዮን በላይ የሆነ ድጋፍ አድርጓል። ዩኒቨርሲቲው በመተከል ዞን በማንዱራ፣ ዳንጉር፣ ጉባ፣ ድባጤ፣ ወንበራ ወረዳዎች እና አጎራባች ወረዳ በሆነው ጓንጓ ወረዳ ለሚገኙ ዜጎች ያደረገውን ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆነ ድጋፍ ለመተከል ዞን አስረከቧል። ድጋፉ አንድ ሚሊየን 7 ሺህ ብር ግምት ያለው ሲሆን፣ 450 ኩንታል የምግብ እህል እና ሌሎች ድጋፎች እንደሚገኙበት በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ ምክትል ፕሬዝዳንት ረዳት ፕሮፌሰር አበራ ባይሳ ተናግረዋል። በድጋፉ ውስጥ የምግብ ማጣፈጫ እህሎች እና ሳሙና እንደሚገኙበትም ገልጸዋል። ዩኒቨርሲቲው ቀጠናውን ለማረጋጋት ለተሰማራው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ለፌዴራል ፖሊስ እና ለክልሉ ፀረ ሽምቅ ኃይል በሬዎች አበርክቷል። በርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙት በ22ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ ብርጌድ ምክትል አዛዥ እና ሎጅስቲክስ ኃላፊ ኮሎኔል ታደሰ ቀልቤሳ፣ አካባቢውን በሚያውኩ ቡድኖች ላይ በጁንታው ኃይል የተወሰደውን ዓይነት እርምጃ እንደሚወሰድ ተናግረዋል። ዩኒቨርሲቲው የተለያዩ ማኅበረሰብ ተኮር አገልግሎቶችን እየሰጠ መሆኑንም ከመተከል ዞን ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply