አሸባሪውና አረመኔው ህወሓት በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ በርካታ ንፁሃንን ጨፈጨፈ! የአማራ ሚዲያ ማእከል ጳጉሜ 2 2013 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ አሸባ…

አሸባሪውና አረመኔው ህወሓት በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ በርካታ ንፁሃንን ጨፈጨፈ! የአማራ ሚዲያ ማእከል ጳጉሜ 2 2013 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ አሸባሪውና አረመኔው ህወሓት በሰሜን ጎንደር ዞን ዳባት ወረዳ ጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ በርካታ ንፁሃንን መጨፍጨፉን የአማራ ክልል መንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ግዛቸው ሙሉነህ አስታወቁ። ወራሪ ኃይል ቀደም ሲል በሰሜን ወሎ እና በአፋር ክልል የፈፀመውን ዓይነት ዘግናኝ ጭፍጨፋ በሰሜን ጎንደር በዳባት ወረዳ በጭና ተክለኃይማኖት ቀበሌ በድጋሚ ፈፅሟል ብለዋል ኃላፊው። በየጫካው እየተፋለሙት ያሉትን ጀግኖች መቋቋም ያልቻለው ወራሪ በየቤታቸው የነበሩ አዛውንቶችን፣ ህፃናትንና እናቶችን በያሉበት፣ ቀሳውስትንም ቤተ ክርስትያን ገብቶ የፍጥኝ በማሰር ጨፍጭፏቸዋል ብለዋል። ይህ ሰይጣናዊ ቡድን በወረራቸው አካባቢዎች በአፋጣኝ ግብአተ መሬቱ እስካልተፈፀመ ድረስ ሌሎች ጭፍጨፋዎችን እንደሚፈፅም ያላቸውን ስጋት ገልፀዋል። “ከሽብር ቡድኑ የግፍ ፅዋ ሕዝባችንን ለመታደግ ማርሻችንን ቀይረን፣ ፍጥነታችንን ጨምረን ከያለበት ግብአተ መሬቱን በመፈፀም ሕዝባችን ልንታደግ ይገባል” ሲሉ ጠሪ አቅርበዋል። ሚዲያዎችም በፍጥነት ቦታው ድረስ ሄደው ይህን እውነት በመዘገብ ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲያውቀው፣ እንዲያወግዘውና ከኢትዮጵያውያን ጋር እንዲቆም እንዲያደርጉ በማኅበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት አሳስበዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል::

Source: Link to the Post

Leave a Reply