አሸባሪውንና ወራሪውን ትህነግ በመፋለም ወቅት ለተሰዉ የደባርቅ ከተማ የትግሉ ሰማዕታት ወጣቶች የጀግና የቀብር ስነ ስርዓት ተደረገላቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 12 ቀን 2013…

አሸባሪውንና ወራሪውን ትህነግ በመፋለም ወቅት ለተሰዉ የደባርቅ ከተማ የትግሉ ሰማዕታት ወጣቶች የጀግና የቀብር ስነ ስርዓት ተደረገላቸው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ መስከረም 12 ቀን 2013 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪውንና ወራሪውን የትሕነግ ቡድን በገጀራ አንገት ለአንገት ተናንቀው ለተሰው የደባርቅ ከተማ የትግሉ ሰማዕታት ወጣቶች ዛሬ መስከረም 12 ቀን 2014 የጀግና የቀብር ስነ_ስርዓት እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገልጧል። በቀብር ስነ_ስነ ስርዓቱም ለጀግኖች ሰማዕታት ወታደራዊ የሰልፍ ስነ_ስርዓት ትዕይንት መካሄዱ ተነግሯል። የጀግኖች የቀብር ስነ_ስርዓት በደባርቅ ከተማ መስቀል አደባባይ ስርዓተ ፍታት ተካሂዶ በደብረ ሳልህ ቅዱስ ሚካኤል ቤቴክርስቲያን በክብር እንዲያርፍ ይደረጋል ተብሏል። በጀግኖች ስርዓተ ቀብር በደባርቅ ከተማ አስተዳደርና እና ወጣቶች የሀገራችን ኢትዬጵያን ህዝብ የአሸናፊነት እና አርበኝነት ታሪክ የሚዘክሩ እንዲሁም ኢትዮጵያዊ አንድነትን የሚያሳዩ መፈክሮች ተዘጋጅተው በደባርቅ ከተማ በመስቀል አደባባይ ተንፀባርቀዋል። በጀግኖች የቀብር ስነ_ስርዓት በጭናና ቦዛ በግፍ የተጨፈጨፎ ንፁሀን ወገኖች ታስበዋል። የደባርቅ_ከተማ_አስተዳደርን ጠቅሶ የከተማው ኮሚዩኒኬሽን እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply