You are currently viewing አሸባሪው ህወሃት በዋግኽምራ ጋዝጊብላ አካባቢ በእንስሳት ላይ ሳይቀር ግፍና በደል እየፈጸመ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ   ጳጉሜ 3 ቀን 2014 ዓ.ም        አዲስ አበባ ሸዋ አሸባ…

አሸባሪው ህወሃት በዋግኽምራ ጋዝጊብላ አካባቢ በእንስሳት ላይ ሳይቀር ግፍና በደል እየፈጸመ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 3 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባ…

አሸባሪው ህወሃት በዋግኽምራ ጋዝጊብላ አካባቢ በእንስሳት ላይ ሳይቀር ግፍና በደል እየፈጸመ ነው። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ጳጉሜ 3 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪው ህዋሃት በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ ጋዝጊብላ ወረዳ ዛሮታ ቀበሌ የአርሶ አደር ንብረት እንስሳቶችን በመግደልና በመዝረፍ ዋነኛ የህዝብ ጠላት መሆኑን አሳይቷል። በወራሪው ቡድን ጉዳት የደረሰባቸው አርሶ አደሮች እንደተናገሩት አርሰን፣ አምርተን ልጅ እናሳድግበታለን፣ ከእርሻ በተጨማሪ ህይወታችን እንመራበታለን እንገለገልባቸዋለን ብለው የሚተማመኑባቸውን በሬ፣ ፍየልና በግ እንዲሁም ዶሮ በአሸባሪ ቡድኑ ተበልቶባቸዋል። ከዚህ በተጨማሪ እንስሳቱን በግፍ በመግደል ከጥቅም ውጭ በማድረግ የአርሶ አደሩን ቅስም ሰብሯል። እንስሳት በመዝረፍና መግደል ቡድኑ ለአርሶ አደሩ ያለውን ከፍተኛ ጠላቻ ያሳየበት ሰይጣናዊ ድርጊት እንደሆነ ተጓጅዎች አስረድተዋል። የወራሪዉ ህዋሃት ዋነኛ አላማው አርሶ አደሩ እንዳያርስ፣ እንዳያመርት በማድረግ ህዝቡን ለችግር፣ ርሀብ፣ ስቃይና መከራ መዳረግና አጠቃላይ ኢኮኖሚውን መጉዳት ነው። ወራሪው ቡድን ከህዝብ ጋር ፀብ የለኝም፣ ጠላቴ የአማራ አመራር ነው እያለ በአፈ ቀላጤዎቹና ሚዲያዎቹ የሚለፍፈው ፍፁም ሀሰት መሆኑን በጭካኔ ተግባሩ አስመስክሯል። ህዋሃት በክፋት ተወልዶ በክፋት ያደገ በከፋቱም ወደ መቃብር እየወረደ ያለ አላማ ቢስ ቡድን እንደሆነ አውቆ የሚሰጠውን የውሸትና የመከፋፈያ ሀሳብ ወደ ጎን ብሎ በአንድነትና በቁርጠኝነት መታገል ያስፈልጋል በማለት አሳስበዋል ተጓጅዎቹ። የጋዝጊብላ ወረዳ ክሙኒኬሽን ነው እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply