አሸባሪው ህወሓት በኮምቦልቻ ማዕከላዊ መጋዝን የነበረ ከ100 ሺህ ኩንታል በላይ የምግብ እህል መዝረፉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 6 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበ…

አሸባሪው ህወሓት በኮምቦልቻ ማዕከላዊ መጋዝን የነበረ ከ100 ሺህ ኩንታል በላይ የምግብ እህል መዝረፉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 6 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪው ህወሓት በኮምቦልቻ ማዕከላዊ መጋዝን ተከማችቶ የነበረ 100 ሺህ ኩንታል በላይ የእርዳታ ምግብ እህል መዝረፉን ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል። የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ እንደገለጹት÷ አሸባሪው ህወሓት በደሴ እና ኮምቦልቻ ከተማ በቆየባቸው ጊዜያት ከፍተኛ የሆነ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት አድርሷል። በዚህ መሰረትም የሽብር ቡድኑ በኮምቦልቻ ማዕከላዊ መጋዝን የነበረና ከ100 ሺህ በላይ ለተፈናቀሉ ዜጎች ለማዋል የተዘጋጀ የምግብ እህል መዝረፉን ተናግረዋል። በኮምቦልቻ ከተማ ኮሚሽኑ 12 መጋዝኖች እንዳሉት የገለጹት ዳይሬክተሩ÷ የሽብር ቡድኑ አባላት በእነዚህ መጋዝኖች የነበሩ የምግብ እህሎችን ሙሉ በሙሉ መዝረፋቸውን አስረድተዋል። አሁን ላይ በእነዚህ መጋዝኖች ምንም ዓይነት የምግብ እህል ክምችት አለመኖሩን ነው አቶ ደበበ የገለጹት። ከዚህ ባለፈም በመጋዝኖቹ ቅጥር ግቢ ውስጥ የነበሩ የኮሚሽኑ ተሽከርካሪዎችን የሚችለውን ወስዶ የቀሩትን እንዳወደመ ጠቁመዋል ሲል ኤፍቢሲ ዘግቧል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply