አሸባሪው ሕወሃት የሮቢት ጤና ጣቢያን ማቃጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። የአማራ ሚዲያ ማእከል መስከረም 25 2015 አ/ም አዲስ አበባ አሸባሪው ሕወሃት ለበርካቶች የሕክምና አገልግሎ…

አሸባሪው ሕወሃት የሮቢት ጤና ጣቢያን ማቃጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናገሩ። የአማራ ሚዲያ ማእከል መስከረም 25 2015 አ/ም አዲስ አበባ አሸባሪው ሕወሃት ለበርካቶች የሕክምና አገልግሎት ይሰጥ የነበረውን የሰሜን ወሎ ዞን ሮቢት ከተማ ጤና ጣቢያን ማቃጠሉን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። የሮቢት ከተማ ነዋሪ ወይዘሮ በላይነሽ አምባው ለበርካታ ጊዜያት ለጤናቸው መላ ያገኙበት የነበረው የሕክምና ጣቢያ በሽብር ቡድኑ ምክንያት መዘረፉንና የተለያዩ ክፍሎቹም መቃጠላቸውን አስረድተዋል። የሽብር ቡድኑ ታጣቂዎች ጤና ጣቢያውን ከማቃጠላቸውና የተለያዩ የሕክምና መሳሪያዎችንና መድኃኒቶች ዘርፈው ከመውሰዳቸው ባለፈ ይዘው መሄድ ያልቻሉትን ደግሞ እያበላሹና እያቃጠሉ አካባቢውን ጥለው መሸሻቸውን ተናግረዋል። ሌላኛዋ የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ አረጋሽ ወርቁ በበኩሏ፤ የትህነግ ታጣቂዎች የሕዝብ መገልገያውን ተቋም አቃጥለው ሲሄዱ የአካባቢው ሕብረተሰብ ተሰባስቦ እሳቱን በውኃና በአፈር በማጥፋት ወደ ሌሎች ክፍሎችም እንዳይዛመት አድርጓል ብላለች። በዚህ የሕብረተሰቡ ጥረት የተነሳ የጤና ጣቢያው ካርድ ክፍልና መረጃ ማደራጃ ክፍሎች ሙሉ በሙሉ መውደማቸውን ተናግራለች። ጤና ጣቢያው በሺዎች የሚቆጠሩ የአካባቢው ነዋሪዎች በአነስተኛ ወጪ የሚገለገሉበት እንደነበር አስታውሳ፤ ወላዶች ህጻናትና አረጋውያንን በማገልገል የሚታወቅ ጤና ጣቢያ እንደሆነ ገልጻለች። ጥፋትን ዓላማ አድርጎ የተነሳው የሽብር ቡድኑ የሕዝብ መገልገያ ማዕከላትን ለይቶ ማውደሙ ደግሞ ምንያክል ለሕዝብ ዴንታ የሌለው የጥፋት መልዕክተኛ መሆኑን በግልጽ ያሳየ ነው ሲሉ አስረድተዋል። የከተማዋ ነዋሪ ወይዘሮ በላይነሽ ደጉ የሽብር ቡድኑ ከሕዝብ መገልገያዎች ባለፈ የነዋሪዎችንም ቤትና ንብረት በመዝረፍ እንዲሁም ንጹሃንን በመግደል አስከፊ ወንጀሎችን መፈጸማቸውን ገልጸዋል። መላው ኢትዮጵያዊ ለተጎዱት ድጋፍ ከመለገስ ባለፈ የሽብር ቡድኑ በንጹሃን ላይ ያደረሰውን በደል ለዓለም በማሳወቅ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ዘገባው የኢፕድ ነው

Source: Link to the Post

Leave a Reply