አሸባሪው ሕወሓት በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዝቋላ ወረዳ የሚገኘውን ቅዳሚት ጤና ጣቢያ ሙሉ በሙሉ ማውደሙ ተገለጸ! መስከረም 02/2015 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) ጦርነት እና ጥፋት ተፈጥሯ…

አሸባሪው ሕወሓት በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዝቋላ ወረዳ የሚገኘውን ቅዳሚት ጤና ጣቢያ ሙሉ በሙሉ ማውደሙ ተገለጸ! መስከረም 02/2015 ዓ.ም (አሻራ ሚዲያ) ጦርነት እና ጥፋት ተፈጥሯዊ ግብሩ የሆነው አሸባሪው ሕወሓት በተደጋጋሚ የሚቀርቡለትን የሰላም አማራጮች በመግፋት በጥፋት ሥራው ቀጥሎበታል፡፡ ለሦስተኛ ዙር በኢትዮጵያ ላይ በከፈተው ጦርነት በአማራ እና አፋር ክልሎች ንጹሐንን በግፍ ጨፍጭፏል፤ የሕዝብ መገልገያ ተቋማትን አውድሟል፤ ዘርፏል፡፡ አሸባሪው ሕወሓት ለሕዝብ ያለውን ጥላቻ እና ንቀት ወረራ በፈጸመባቸው አካባቢዎች በተግባር አሳይቷል፡፡ አሸባሪው ሕወሓት በዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዝቋላ ወረዳ ቅዳሚት ከተማ በፈጸመው ወረራ ንጹሐንን በግፍ ገድሏል፤ አፈናቅሏል፤ ዘረፋ እና ውድመት ፈጽሟል፡፡ በከተማው የሚገኙ የቅዳሚት ጤና አጠባበቅ ጣቢያ እና የአንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን አውድሟቸዋል። የቅዳሚት ከተማ ነዋሪ ቄስ ሳኅሌ ወልዴ እንዳሉት አሸባሪው ሕወሓት ቅዳሚት ከተማን በወረረበት ወቅት በጤና ጣቢያው የህሙማን መተኛ አልጋዎችን ሳይቀር ሌሎች ንብረቶችን በእሳት አቃጥሏል ብለዋል። የተቀረውን የተቋሙን ንብረቶች ደግሞ መዝረፉን ተናግረዋል። ሌላኛው አስተያየት ሰጪ መምህር ላቀው ብሩ አሸባሪው ሕወሓት የሕዝብ መገልገያ ተቋማትን ሳይቀር ገነጣጥሎ ለማገዶነትና ለምሽግ መሥሪያ እንዳዋላቸው ገልጸዋል፡፡ ይህም የአሸባሪ ቡድኑን ዓላማና የሕዝብ ጠላትነትን የሚያሳይ ነው ብለዋል። የዝቋላ ወረዳ ምክትል አሥተዳዳሪና የጤና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ እስጢፋኖስ ወንዳዬ አሸባሪው ሕወሓት በዝቋላ ወረዳ በስድስት ቀበሌዎች በወረራ በቆየባቸው ወራት በሕዝቡ ላይ ከባድ ግፍና በደል ፈፅሟል ነው ያሉት። አሸባሪው ቡድኑ በቅዳሚት ከተማ የሚገኙ ለሕዝብ አገልግሎት በሚሰጠው ጤና ጣቢያ ላይ ከባድ ዘረፋና ውድመት ማድረሱን ለአብነት አንስተዋል፡፡ አሁን አገልግሎት መስጠት ይጀምር ቢባል እንኳን እንደ አዲስ ከሕንጻዎቹ ጀምሮ መሠራት የሚጠይቅ ነው ብለዋል። የመንግሥት እና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች አገልግሎት መስጫ ተቋማቱን መልሶ ለመገንባት ያላሰለሰ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል ሲል አሚኮ ዘግቧል። ለፈጣንና አዳዲስ መረጃዎች አሻራ ሚዲያ የአይበገሬዎቹ ልሳን:- Youtube:- https://www.youtube.com/channel/UCPmgFzP2ZPmdGjHxXjigJaw Facebook:- https://www.facebook.com/asharamedia24 ቴሌግራም:- https://t.me/asharamedia24

Source: Link to the Post

Leave a Reply