አሸባሪው ሸኔ የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ቤተሰብን ጨምሮ 8 ሰላማዊ ሰዎችን ገደለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 17 ቀን 2014 ዓ.ም…

አሸባሪው ሸኔ የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ቤተሰብን ጨምሮ 8 ሰላማዊ ሰዎችን ገደለ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 17 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪው ሸኔ የቀድሞ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ 3 ወንድሞችን ጨምሮ 8 ሰላማዊ ሰዎችን ጭካኔ በተሞላበት መንገድ መግደሉን የዞኑ አስተዳደር አስታውቋል። የሽብር ቡድኑ ይህን ግፍ የፈፀመው በጅማ ዞን ኖኖ ቤንጃ ወረዳ ኮንቺ ቀበሌ ታኅሣሥ 15 ቀን 2014 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:30 አካባቢ መሆኑ ተገልጿል። በአሸባሪው ቡድን የተገደሉት የአቶ ዓለማየሁ አቶምሳ ቤተሰብ አባላት አቶ አደባ አቶምሳ፣ አቶ ቲሊንቲ አቶምሳ እና አቶ ሙላቱ አቶምሳ የተባሉ ወንድሞቻቸው መሆናቸውን የቤንጃ ወረዳ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ በሬቻ ተኩ ለኦቢኤን ተናግረዋል። የቀድሞው የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ዓለማየሁ አቶምሳ የኦሮሞ ሕዝብ የነፃነት ትግልን ካቀጣጠሉት እና የአሸባሪው ህወሓት ውድቀት እንዲፋጠን ምክንያት ከሆኑ ሰዎች መካከል አንዱ ናቸው። የደረሰብን ኀዘን ከባድ ነው ያሉት አቶ በሬቻ ተኩ፣ ከአቶ ዓለማየሁ ቤተሰብ በተጨማሪ ሌሎች ሰላማዊ ሰዎችም በጭካኔ መገደላቸውን እና ከእነዚህም መካከል ሁለቱ ሴቶች መሆናቸውን ተናግረዋል። አሸባሪው ሸኔ የአርሶ አደሩን ሀብት ንብረት ማቃጠሉን እና የተረፈውም ጥቅም ላይ እንዳይውል መበታተኑን ተናግረዋል። 17 የአርሶ አደሮች ቤት በዚሁ ቡድን በመቃጠሉ ምክንያት የተፈናቀሉ ሰዎች መኖራቸውን ገልጸዋል። ካቃጠሉት የአርሶ አደሩ ሰብል መካከል 9 ጎተራ በቆሎ እና በርካታ የጤፍ ክምር እንደሚገኝ የገለጹት ምክትል አስተዳደሩ፣ በሚያሳዝን መልኩ ጥገት ላምን እና ጥጆችን ጨምሮ ወደ በረት አስገብተው አቃጥለዋል ብለዋል። የኖኖ ቤንጃ ወረዳ ነዋሪዎች የአሸባሪው ሸኔን ድርጊት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ መውጣታቸውም ተገልጿል። ኢቢሲ እንደዘገበው።

Source: Link to the Post

Leave a Reply