You are currently viewing “አሸባሪው በደብረ ዘቢጥ የተደመሰሱበትን አመራሮች አንገታቸውን በመቅላት አስከሬናቸውን ደብቆ ሸሽቷል”:-  የዐይን እማኞች የአማራ ሚዲያ ማእከል ነሀሴ 27 2013 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵ…

“አሸባሪው በደብረ ዘቢጥ የተደመሰሱበትን አመራሮች አንገታቸውን በመቅላት አስከሬናቸውን ደብቆ ሸሽቷል”:- የዐይን እማኞች የአማራ ሚዲያ ማእከል ነሀሴ 27 2013 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵ…

“አሸባሪው በደብረ ዘቢጥ የተደመሰሱበትን አመራሮች አንገታቸውን በመቅላት አስከሬናቸውን ደብቆ ሸሽቷል”:- የዐይን እማኞች የአማራ ሚዲያ ማእከል ነሀሴ 27 2013 ዓ/ም አዲስ አበባ ኢትዮጵያ አሸባሪው ህወሓት በደብረ ዘቢጥ ግምባር በተወሰደበት እርምጃ የተደመሰሱበትን የጦር አመራሮች አንገታቸውን በመቅላት አስከሬናቸውን ደብቆ መሸሹን በግምባሩ ላይ የነበሩ የዓይን እማኞች ገልጸዋል፡፡ በደብረ ዘቢጥ ግምባር ላይ የነበሩ ያይን እማኞች ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት መረጃ፤ በአውደ ውጊያው አሸባሪው ቡድን የጦር አመራሮቹ ሲደመሰሱበት አንገታቸውን ቆርጦ በመደበቅ እንደሚሸሹ ተናግረዋል፡፡ እንደ ሻምበል ጌታሁን ገለጻ የአሸባሪው ቡድን ከዚህ ቀደም በነበረው የህግ ማስከበር ዘመቻ ወቅት አዋጊዎቹ ሲሰው ማንነታቸው ይፋ እንዳይወጣ አንገታቸውን ይቆርጥና ይደብቅ ነበር፡፡ በህልውና ዘመቻ ወቅትም ተመሳሳይ ድርጊት በመፈጸም በተለይም በደብረ ዘቢጥ ግምባር የተሰውበትን በርካታ የጦር አመራሮች አንገታቸውን በመቁረጥ እጅግ አስነዋሪ ተግባር እየፈጸመ ይገኛል፡፡ ይህ የጠላት ቡድን ህጻናትን ፊት ለፊት በማሰለፍ እያስፈጃቸው ነው ያሉት ሻምበል ጌታሁን፤ በግምባሩ በኢትዮጵያ ሰራዊት በተወሰደበት ከፍተኛ ጥቃት በርካታ የጦር መሪዎቹም ተደምስሰውበታል፤ እውነቱ ይፋ እንዳይወጣ በሚልም የለመደውን አንገት የመቁረጥ ተግባር መፈጸሙን ገልጸዋል፡፡ የሚሊሻ ቡድኑን ተቀላቅሎ በደብረ ዘቢጥ በግምባር ለውጊያ የተሰለፈው ሰፊው በቀለ የጦር አመራሮቹ ጭምር እየተመቱ እንዳሉና በተለይም የተሰውበትን አመራሮች ዘግናኝና ኢ-ሰብዓዊ በሆነ መልኩ አንገታቸውን በመቅላት ማንነታቸው እንዳይታወቅ በማድረግ ጥለው ከሸሿቸው አስከሬኖች መመልከቱን ገልጿል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply