አሸባሪው ቡድን ያደረሰው ውድመት በጦር ወንጀል የሚያስጠይቀው ነው -ጎንደር ዩኒቨርስቲ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3፣ 2014  አሸባሪ ቡድኑ በደቡብ ጎንደር ያደረሰው ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት በጦር ወንጀል የሚያስጠይቀው ነው ሲሉ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ኃላፊ አቶ ልጅ አለም ጋሻው ገለጹ፡፡

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የህግ ትምህርት ቤት ኃላፊና በደቡብ ጎንደር አሸባሪው ቡድን ያደረሰውን ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት የሚያጣራው የጥናት ግብረ ኃይል ሰብሳቢ አቶ ልጅ አለም ጋሻው ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንደተናገሩት፣ የህወሓት አሸባሪ ቡድን ለዘጠኝ ቀናት ወሯቸው በነበሩ የደቡብ ጎንደር ሦስት
ወረዳዎችና የገጠር ቀበሌዎች የተደራጀ፣ የተጠና፣ ሰብዓዊና ቁሳዊ ውድመት ማድረሱን በጥናት መረጋገጡን ገልጸዋል።

አቶ ልጅ አለም አሸባሪ ቡድኑ ጥቃቱን ለመፈጸም ከተማዎችን የገጠር ቀበሌዎችን፣ መንደሮችን በወረራ ሲይዝ የማሸበር፣ የማግባባት፣ የመዝረፍ እና የማውደም ስልቶችን መጠቀሙን በጥናት ተለይቷል። ህዝብ በሰፈረባቸው ቦታዎች ላይ ቀላልና ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ ንጹሃን ዜጎች ላይ ጥቃት በማድረስ ሽብር በመፍጠር አካባቢዎችን በቀላሉ መቆጣጠር የመጀመሪያው ስልት ማድረጉን ገልጸዋል።

መኖሪያ ቀያቸውን የለቀቁ ሰዎችን በመሰብሰብ ከህዝብ ጋር ምንም አይነት ችግር እንደሌለበት ሰላማዊ እንደሆነና ጠባችን ከጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ጋር ነው በማለት ህዝቡ ሰላማዊነታቸውን እንዲረዳና ጥቃት እንደማያደርስባቸው በማግባባት ካታለለ በኋላ በርካቶችን በጠራራ ጸሃይ መፍጀቱን ተናግረዋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply