You are currently viewing አሸባሪው ትሕነግ በአማራ ላይ የፈጸመውን ወረራ ተከትሎ በደሴ ከተማ ብቻ ከተለያዩ ተቋማት ከ1,000 በላይ ቅርሶች ተዘርፈዋል፤ ለማስመለስም አልተቻለም ተብሏል፡፡  አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

አሸባሪው ትሕነግ በአማራ ላይ የፈጸመውን ወረራ ተከትሎ በደሴ ከተማ ብቻ ከተለያዩ ተቋማት ከ1,000 በላይ ቅርሶች ተዘርፈዋል፤ ለማስመለስም አልተቻለም ተብሏል፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

አሸባሪው ትሕነግ በአማራ ላይ የፈጸመውን ወረራ ተከትሎ በደሴ ከተማ ብቻ ከተለያዩ ተቋማት ከ1,000 በላይ ቅርሶች ተዘርፈዋል፤ ለማስመለስም አልተቻለም ተብሏል፡፡ አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሀምሌ 14 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪው ትሕነግ በአማራ ላይ የፈጸመውን ወረራ ተከትሎ በደሴ ከተማ ብቻ ከተለያዩ ተቋማት ከ1,000 በላይ ቅርሶች ተዘርፈዋል፤ ለማስመለስም ስላለመቻሉ ተገልጧል። በደሴ መርሆ ግቢ ቤተ መንግስት ከተዘረፉ 529 ቅርሶች እስካሁን አንዱንም ለማስመለስ አልተቻለም ተብሏል። ከደሴ ሙዝዬም ከተዘረፉ ቅርሶች የተወሰኑት ከደሴ ሙዝዬም ደጃፍ ተጥለው መገኘታቸው ተገልጧል፤ ያልታወቀ ግለሰብ ሌሊቱን ቅርሶችን ከሙዚዬሙ ደጃፍ አስቀምጦ ስለመሄዱ ተነግሯል። በሰሜኑ ጦርነት ከፍተኛ ጉዳት፣ ውድመትና ዝርፊያ ከተፈጸፈመባቸው ከተሞች የደሴ ከተማ አንደኛው ነው። በከተማው የበርካታ ቅርሶች መገኛ የነበሩት የደሴ ሙዝዬም፣መርሆ ግቢ፣የልዑል አስፋ ወሰን ኃይለ ስላሴ ቤተ መንግስት የከፋ ዝርፊያ እና ውድመት የደረሰባቸው መሆኑ ይታወሳል። በአፄ ቴዎድሮስ እና በአፄ ምኒልክ የንግስና ዘመን መገልገያ የነበሩ ቅርሶች በሙዝዬሙ ተከማችተው ይገኙና ይጎበኙም እንደነበር ይታወቃል። ሸገር ያነጋገራቸው የደሴ ሙዝዬም የልማት ቡድን መሪ አቶ መረሳ ይርጋ ከመርሆ ቤተ መንግስት የተዘረፉት ታሪካዊ ቅርሶች 529 መሆናቸውን እና እስካሁን አንዱንም ለማስመለስ አልተቻለም ብለዋል። ከደሴ ሙዝዬም ብቻ የተዘረፉት ቅርሶች ደግሞ ከ490 በላይ ናቸው ያሉት አቶ መረሳ 18ቱ ተመልሰዋል ብለዋል። በአጠቃላይ አሸባሪው ትሕነግ በአማራ ላይ የፈጸመውን ወረራ ተከትሎ በደሴ ከተማ ብቻ ከተለያዩ ተቋማት የተዘረፉ ከ1,000 በላይ ቅርሶችን ለማስመለስ እየጣሩ መሆናቸውንና በፈቃደኝነት ቅርሶችን ለማስመለስ ከሚደረገው ጥረት ባሻገር በተመጣጣኝ ዋጋ በመግዛት ለመረከብም ስለመታሰቡ ተገልጧል። ዘገባውን ለማጠናቀር ሸገርን በምንጭነት ተጠቅመናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply