አሸባሪው ትሕነግ በአፆኪያ ገመዛ የጅምላ ግድያ መፈፀሙ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 26 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪው ትሕነግ በሰሜን ሸዋ ዞን አ…

አሸባሪው ትሕነግ በአፆኪያ ገመዛ የጅምላ ግድያ መፈፀሙ ተገለፀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 26 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪው ትሕነግ በሰሜን ሸዋ ዞን አፆኪያ ገመዛ ወረዳ አንቦ ውሀ ቀበሌ ላይ የጅምላ ግድያ መፈፀሙ ተገልጧል። እስካሁን ባለው መረጃ 70 የሚደርሱ ንፁሀን (ከአምስት ዓመት ህፃን ጀምሮ አዛውንቶችና የአዕምሮ ታማሚ ሳይቀር) የጅምላ ግድያው ሰለባ ሆነዋል። የጅምላ ግድያው የተፈፀመው ኅዳር 24 ሲሆን ጉዳት የደረሰባቸው ተጎጅዎች ዛሬም እየሞቱ መሆኑንና ወደቀብር ሲሄዱ ዋልታ በቦታው ሆኖ ተመልክቷል። በአንድ መቃብር ላይ ብቻ እስከ 51 የሚደርሱ የጅምላ ግድያ ሰለባዎች እንደተቀበሩ የቀበሌዋ ነዋሪ የአይን እማኞች ተናግረዋል። ምክንያቱ ደግሞ ወደ ህክምና ለመውሰድ አካባቢው በሽብር ቡድኑ ከበባ ውስጥ መሆኑ ነው። የሟቾች ቁጥር እስከ 100 ሊደርስ እንደሚችል የጉዳቱ ሰለባ ቤተሰቦች ለዋልታ ተናግረዋል። የጅምላ ግድያውን የፈፀመው የሽብር ቡድኑ ተረፈ ጁንታ በማህል ሜዳ እና ማጀቴ አካባቢ ድባቅ ተመቶ በሰሜን ሽዋ አፆኪያ ገመዛ ወረዳ አንቦ ውሀ ባለ ጫካ ለማለፍ ሲሞክር የአካባቢው ሚሊሻ አላሳልፍ ብሎ ስለገታውና ሙትና ቁስለኛ በማድረጉ ከመደምሰስ የተረፈው የሽብር ቡድኑ ቅሬት በአንቦ ውሃ ቀበሌ ንፁሃን ላይ የበቀል በትሩን አሳርፏል። አሸባሪው የትሕነግ ወራሪ ኃይል በማይካድራ፣ በጭና ተክለ ሀይማኖት፣ በአጋምሳ፣ በጋሊኮማና ሌሎችም የፈፀመውን የጅምላ ግድያ በአፆኪያ ገመዛ ወረዳ የአንቦ ውሀ ቀበሌ ላይ በመፈፀም ለሰው ልጀ ሁሉ ጠላትነቱን አስመስክሯል ሲል ዋልታ ቲቪ ዘግቧል፡፡

Source: Link to the Post

Leave a Reply