አሸባሪው ትሕነግ እና ኦነግ ሸኔ የከፈቱትን ግልጽ ጦርነት ለመቀልበስ በተደረገው ተጋድሎ በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ተሰልፈው ሲታገሉ ቆስለው በደብረ ዘይት መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኮሌጅ ግቢ ለሚ…

አሸባሪው ትሕነግ እና ኦነግ ሸኔ የከፈቱትን ግልጽ ጦርነት ለመቀልበስ በተደረገው ተጋድሎ በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ተሰልፈው ሲታገሉ ቆስለው በደብረ ዘይት መከላከያ ኢንጅነሪንግ ኮሌጅ ግቢ ለሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የምሳ ግብዣ ተደረገ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ታህሳስ 19 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪው ትሕነግ እና ኦነግ ሸኔ የከፈቱትን ግልጽ ጦርነት ለመቀልበስ በተደረገው ተጋድሎ በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ተሰልፈው ሲታገሉ ቆስለው በደብረ ዘይት መከላከያ ዩኒቨርስቲ ኢንጅነሪንግ ግቢ ለሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት አባላት የማዕድ ማጋራት መደረጉን አሚማ በስፍራው ተገኝቶ ተመልክቷል። በመከላከያ ዩኒቨርስቲ ኢንጅነሪንግ ኮሌጅ በማዕድ ማጋራቱ ወቅትም በጎ ፈቃደኛ ባለሃብቶችን ያስተባበረው የለሚኩራ ክ/ከ የዋና ስራ አስፈጻሚ ም/ስራ አስኪሂያጅ አቶ ዳዊት ወ/እየሱስ በቦታው የተገኙት ሀገር ለማፍረስ የሚንቀሳቀሱ አሸባሪ ኃይሎችን ለመከላከል ብለው ሲዋደቁ የቆሰሉ ጀግኖችን ለመጠየቅ ነው ብለዋል። ከአሁን ቀደምም ወደ ግንባር በመሄድ ለወገን ጦር ድጋፍ አንድ አይሉ ሁለት ጊዜ ድጋፍ ማድረጋቸውን ገልጸው በቀጣይም እንደ ለሚኩራ ክ/ከተማ አጠናክረው እንደሚቀጥሉበት ገልጸው፣ ለሚዋደቁ ጀግኖችም ምስጋና አቅርበዋል። ከመከላከያ ዩኒቨርስቲ የኢንጅነሪንግ ኮሌጅ የሰው ኃብት ልማት ተጠሪ ኮሎኔል አብዱልቃድር በማገገሚያ ክፍሉ ያሉ የሰራዊት አባላት እንዲያገግሙ ለተደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል። ወጣቶች ከከፈሉልን መስዋዕትነት አኳያ ድጋፍ ማድረግ ውዴታ ሳይሆን ግዴታችን መሆኑንም ተናግረዋል። በቀጣይም ከጁንታዎች ጋር ሲፋለሙ ለቆሰሉ ጀግኖች ከሚደረገው የምግብ እና ሌሎች አስፈላጊ ግብአቶች በተጨማሪ ተደራጅተው በመምጣት ገላቸውን እና ልብሳቸውን በማጠብ አብሮነታቸውን እንዲያሳዩም ጥሪ አድርገዋል። የማዕድ ማጋራቱን ካደረጉት ባለሃብቶች መካከል አንዱ አቶ መኩሪያ ደርቤ ይባላሉ፤ ነዋሪነታቸው በአዲስ አበባ የካ አባዶ 13 አካባቢ ነው። በእያመቱ የቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ በዓልን ሲያከብሩ ለተቸገሩ ወገኖች ድጋፍ ማድረግ የተለመደ ተግባራቸው መሆኑን ይገልጣሉ። ይህ ሰብአዊ ድጋፍ በአዘቦትም ሆነ በበዓላት ወቅት መለመድ ያለበት በጎ ተግባር መሆኑን የገለጹት አቶ መኩሪያ ሀገርን ለማፍረስ የተነሱ አሸባሪዎችን ሲፋለሙ ለቆሰሉ ጀግኖች አብሮነቴን ለመግለጽ አቅሜ በፈቀደ መጠን የምሳ ግብዣ አድርጌያለሁ ብለዋል። የአቶ መኩሪያ ደርቤ ባለቤት ወ/ሮ ስንታየሁ ደሳለኝ በበኩላቸው የቅዱስ ገብርኤልን በዓል ስለሀገር እና ስለወገን ሲሉ ዋጋ እየከፈሉ ያሉ ጀግኖችን በማስታዎስ የምሳ ግብዣ በማድረጋችን ደስታ ይሰማናል ብለዋል። ሀገር እና ወገን ለመታደግ በአማራ እና በአፋር የተለያዩ አካባቢዎች ግልጽ ጦርነት የከፈቱ አገር አፍራሾችን በመመከት ብሎም በመቀልበስ እና ድባቅ በመምታት ረገድ ሌት ተቀን እየታገሉ ለሚገኙ የመከላከያ ሰራዊት፣ የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖ እና ሚሊሻ ሁሉም የሚችለውን በመደገፍ አብሮነቱን መግለጽ አለበት የሚል መልዕክትም አስተላልፈዋል። በጥየቃው የተገኙት ኢንስፔክተር ኃይሉ ሽፈራው በበኩላቸው ትግሉ የጋራ በመሆኑ አንድ ሆነን ጀግኖቻችን መደገፍ እና መጠየቅ እንደሚገባን ነወወ ጥሪ ያቀረቡት። በለሚኩራ ወረዳ 14 የቅዱስ ገብርኤል ሆቴል ባለቤት አቶ አስራት ህሩጰ እና የአላዶር ሆቴል ባለቤት ተካልኝ በዛብኝ ከአሸባሪዎች ጋር ሲፋለሙ ለቆሰሉ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ማዕድ ያጋሩ ሲሆን በስፍራው ተገኝተው ታጋዮች ያሉበትን ሁኔታ ሲያዩ ከእነ ወኔያቸው በመሆናቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል። ኢትዮጵያዊያን ኩራት ሊሰማን እንደሚገባ መለረካም ስራን ማስቀደም እንዳለብንም ጠቁመዋል። ክብር ስለእኛ ሲሉ ለሚዋደቁ ጀግኖች ሰማዕታት ይሁን! አሚማ በደብረ ዘይት መከላከያ ዩኒቨርስቲ ኢንጅነሪንግ ኮሌጅ ተገኝቶ የተደረገውን ድጋፍ ተመልክቷል፤ ሙሉ ዝግጅቱን በዩቱብ አድራሻው ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply