You are currently viewing አሸባሪው ትሕነግ “ከአፋር መሬት ሙሉ በሙሉ ለቅቄ ወጥቻለሁ” በማለት የሚያሰራጨው ወሬ የውሸት ፕሮፖጋንዳ ነው” ሲል የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

አሸባሪው ትሕነግ “ከአፋር መሬት ሙሉ በሙሉ ለቅቄ ወጥቻለሁ” በማለት የሚያሰራጨው ወሬ የውሸት ፕሮፖጋንዳ ነው” ሲል የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ…

አሸባሪው ትሕነግ “ከአፋር መሬት ሙሉ በሙሉ ለቅቄ ወጥቻለሁ” በማለት የሚያሰራጨው ወሬ የውሸት ፕሮፖጋንዳ ነው” ሲል የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ሚያዝያ 20 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ “ጁንታው ከአፋር መሬት ሙሉ በሙሉ ለቅቄ ወጥቻለሁ” በማለት የሚያሰራጨው ወሬ የውሸት ፕሮፖጋንዳ ነው ሲል የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አስታውቋል። የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ባወጣው መግለጫው አሸባሪው ህወሀት በከባድ መሳሪያ በመታገዝ ከወረራቸው በአፋር ክልል የኪልበቲ ረሱ ዞን ወረዳዎች ሙሉ በሙሉ ወጥቻለሁ በማለት ከሰሞኑ ከእውነት የራቀ የሀሰት የማደናገሪያ ፕሮፖጋንዳ በማሰራጨት ላይ ይገኛል ብሏል። በከባድ መሳሪያ በመታገዝ በንፁሃን ላይ ከባድ ድብደባ በመፈፀም የኪልበቲ ረሱ ዞን ወረዳዎችን:_ መጋሌ ወረዳ፣ አብአላ ወረዳ፣ አብአላ ከተማ አስተዳድር፣ ኤረብቲ ወረዳ፣ በራህሌ ወረዳና ኮነባ ወረዳን በሀይል በመቆጣጠር የዘር ማጥፋት በመፈፀም፣ የአካል ጉዳት በማድረስ፣ ከቤት ንብረት በማፈናቀል እና የግለሰቦችና የህዝብ ሀብትና ንብረት ላይ ከባድ ዝርፊያ እና ውድመት ያደረሰ መሆኑን አውስቷል። ጁንታው እያካሄደ ያለው ጦርነት የፖለቲካ አጀንዳ ብቻ ሳይሆን ጦርነቱ ወደ ሃይማኖት ጦርነት እንዲቀየር ቁርአን በማቃጠል፣ መስጂዶችን በማውደም ሙከራ ማድረጉን፣ ከዚያም አልፎ ለዘመናት አብረው የኖሩ የአፋር እና የትግራይ ህዝብ በዘር እንዲጣሉና ጦርነቱ የብሄር ጦርነት እንዲሆን ብርቱ ጥረት ቢያደርግም ይህ እኩይ ሀሳባቸው እንዳይሳካ የአፋር ህዝብና መንግስት ትልቅ ትግል አድርገዋል ነው ያለው። ቡድኑ በኪልበቲ ረሱ በቁጥጥሩ ስር ባደረጋቸው ወረዳዎች ለማሰብ የሚዘገንኑ እጅግ አረመኔያዊ የሆነ ጭካኔ የተሞላበት በከባድ መሳሪያ ንጹሀን ሴቶችን፣ ህጻናትና አዛውንቶችን በጅምላ በመጨፍጨፍ፣ ከ500 ሺህ በላይ ዜጎች ከቀያቸው እንዲፈናቀሉ ያደረገ መሆኑን ጠቅሷል። የከባድ መሳሪያውን ድብደባ በማጠናከርም ለከባድ እንግልትና ስቃይ እንዲዳረጉ በማድረግ:_ 1) በሀብትና ንብረት ላይ የተቀናጀ የሆነ ዝርፊያና ውድመት በመፈፀም፣ 2) በግለሰቦች መኖሪያ ቤቶች ላይ፣ የንግድ ተቋማት ላይ፣ 3) የሀይማኖት ተቋማት ላይ፣ 4) እንዲሁም የህዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማት በተለይም በሆስፒታልና የጤና ተቋማት፣ በትምህርት ቤቶችና ሌሎች ተቋማት ከጥቅም ውጭ እንዲሆኑ አድርጓል። በውስጡ ያለውን ንብረትም በሙሉ በመዝረፍና በማውደም መረጃዎችን በማጥፋት፣ በመጓጓዣ መጫን የሚፈልጉትን ጭኖ በመውሰድ፣ ያልፈለጉትን ደግሞ እልህ በተሞላበት ሁኔታ በማውደም አሸባሪው ህወሀት የአፋር ህዝብ ቀንደኛ ጠላትነቱን በማስመስከር አሁን ላይ ደግሞ “ከያዝናቸው አካባቢዎች ሙሉ በሙሉ ለቅቀናል’ በማለት የተካነበትን ነጭ ውሸት እያሰራጨ እንደሚገኝ ገልጧል። ይህ ቡድን የተካነበትን የማደናገሪያ የውሸት ፕሮፖጋንዳ በመንዛት አካባቢውን ሙሉ በሙሉ ለቅቄያለሁ በማለት በህዝብ ላይ እያደረሰ ያለውን ስቃይ በማራዘም ቀጠናውን አሁንም እንዳይረጋጋ፣ የሰብአዊ ድጋፍ በሚፈለገው መልኩ እንዳይደርስ እንቅፋት ለመሆን እና ርሃብን ለርካሽ ፖለቲካቸው ትርፍ መጠቀሚያ በማድረግ ስለመቀጠላቸው “ከአፋር ሙሉ በሙሉ ወጥተናል” የሚለው ፕሮፖጋንዳቸው ማሳያ ነው። በመሆኑም የፌደራል መንግስትም ሆነ አለም አቀፉ ማህበረሰብ የዚህን እኩይ ቡድን ሴራ በቅጡ በመረዳት ቡድኑ የአካባቢው ሰላም እና መረጋጋት እንዲመለስ ቁርጠኛ አለመሆኑና ለዚህም ሀላፊነቱን አሸባሪው ህወሀት የሚወሰድ መሆኑ ሊታወቅ ይገባል። የአለም ህብረተሰብ ጁንታው በአፋር ህዝብ ላይ ያደረሰውን የዘር ማጥፋትና ግፍ እና በደል በአግባቡ እንዲገነዘብ ሰፊ ጥረቶች የተደረጉ ሲሆን አመርቂ የሆኑ ውጤቶችን በማስገኘትም ላይ እንደሚገኝም የክልሉ መንግስት አስታውቋል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply