You are currently viewing አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በሸዋ ደራ ቆሮ ጉንዶ በርበሬ በተባለ ቀበሌ አባት እና ልጅን እና የ70 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ በርካታ አማራዎችን መግደሉ፣ ማገቱ፣ ከፍተኛ ሀብት ንብረትን መዝረፉ እና…

አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በሸዋ ደራ ቆሮ ጉንዶ በርበሬ በተባለ ቀበሌ አባት እና ልጅን እና የ70 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ በርካታ አማራዎችን መግደሉ፣ ማገቱ፣ ከፍተኛ ሀብት ንብረትን መዝረፉ እና…

አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በሸዋ ደራ ቆሮ ጉንዶ በርበሬ በተባለ ቀበሌ አባት እና ልጅን እና የ70 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ በርካታ አማራዎችን መግደሉ፣ ማገቱ፣ ከፍተኛ ሀብት ንብረትን መዝረፉ እና ማቃጠሉ ተነገረ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 7 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በሸዋ ደራ ቆሮ ጉንዶ በርበሬ በተባለ ቀበሌ አባት እና ልጅን እና የ70 ዓመት አዛውንትን ጨምሮ በርካታ አማራዎችን መግደሉ፣ ማገቱ፣ ከፍተኛ ሀብት ንብረትን መዝረፉ እና ማቃጠሉን የደራ አማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴ ሰብሳቢ መ/ር ኃይለ ሚካኤል አርዓያ ለአማራ ሚዲያ ማዕከል (አሚማ) ተናግረዋል። የሽብር ቡድኑ ህዳር 4/2015 በቆሮ ጉንዶ በርበሬ ቀበሌ ልዩ ስሙ ድሬ ጅላ መድኃኒያለም ጎጥ ላይ ብቻ የአንድ ቤተሰብ እና የአንድ መንደር አባላትን መጨፍጨፉ እና ከፍተኛ ዝርፊያም መፈጸሙ ተገልጧል። የኦነግ ሸኔ የሽብር ቡድን በአማራዎች መኖሪያ ቤታቸው ውስጥ በመግባት በጥይት ከገደላቸው መካከልም:_ 1) አቶ አሰፋ ጌታነህ ከእነ ወንድ ልጃቸው፣ 2) አቶ በላይነህ ታመነ የተባሉ የ70 ዓመት አዛውንት፣ 3) አቶ ግዴለው ታደሰ እና 4) አቶ ሰይድ አሰፋ ይገኙበታል። በአካባቢው የመኖሪያ ቤታቸውን ካቃጠሉባቸው በርካታ አማራዎች መካከልም:_ 1) ምሳዬ በቀለ፣ 2) ፖሊስ ጠና፣ 3) ታደለ ጠና፣ 4) እታለማሁ ጠና፣ 5) ሸጋው ንጉሴ፣ 6) ይትባረክ ተስፋዬ፣ 7) ጤና ተገኘ፣ 😎 እንደሻው ለገሰ፣ 9) እናት ለገሰ፣ 10) ሰጡ ለገሰ፣ 11) ጠጄ ንጉሴ፣ 12) ሙሉጌታ አይተንፍሱ እና 13) አባትልኝ አሰፋ ይጠቀሳሉ። ቤታቸው ከእነ ሙሉ ቤት እቃቸው እና ከተሰበሰበ እና ከከረመ ምርታቸው ጋር እንዲወድምባቸው አድርጓል። ከመካከላቸውም አቶ ሙሉጌታ አይተንፍሱ የተባሉ አባት መኖሪያ ቤታቸው እና ከእነ 30 ኩንታል ጤፍ በሽብር ቡድኑ ተቃጥሎባቸዋል። ህዳር 5ለ6/2015 መከላከያ ሰራዊት ኦፕሬሽን ለመስራት በሚል ወደ ገጠር መውጣቱን ተከትሎ ጥሎን ሄዷል በሚል በመረጃ ክፍተት ምክንያት በርካታ ሴቶች እና ህጻናት ከኦነግ ሸኔ ጥቃት ራሳቸውን ለማትረፍ ሲሉ በመደናገጥ ወደ መርሃቤቴ እና ሬማ ሲሸሹ መስተዋላቸውን የአሚማ ምንጮች ተናግረዋል፤ በከተማዋም የፌደራል ፖሊስ መኖሩ ተገልጧል። በተያያዘም ቡድኑ ህዳር 4/2015 የጎዴ ቄሴ ማህበረ በኩር ገዳምን ሁለት እረኞችን አግቶ መውሰዱን በተጨማሪም የገዳሙን 33 የቀንድ ከብቶችንም አግቶ ወስዷል ሲሉ መ/ር ኃይለ ሚካኤል ገልጸዋል። እስካሁን ታግተው የተወሰዱትን የደራ ነዋሪዎችን በትክክል ለማወቅ አስቸጋሪ መሆኑን የሚናገሩት መ/ር ኃይለ ሚካኤል ህዳር 6/2015 ምሽት ላይ ተለቀዋል ከተባሉት ታጋቾች መካከልም:_ 1) ቄስ እስጢፋኖስ ደጀኔ ተለቀዋል። ምን ያህል ገንዘብ እንደከፈሉ አልታወቀም ተብሏል። 2) ኢ/ር አብቴ ግዴለም፣ ዳምጠው አብቴ የተባለው ልጁ ለአባቱ እንዲከፍል የተጠየቀውን 200 ሽህ ብር ይዞ በሄደበት ልጁንም በማገት 200 ሽህ ብር በመጨመር በድምሩ 400 ሽህ ብር በማስከፈል የለቀቋቸው መሆኑ ተሰምቷል። እስከ ግማሽ እና አንድ ሚሊዮን ብር ድረስ እንዲከፍሉ የተጠየቁ ታጋቾች እንዳሉም ተገልጧል። የታጋቾች ቁጥር ከአሁንበቀደም ከ50 በላይ ተብሎ ቢገለጽም የማጣራት ሂደቱ እንዳመለከተው ቁጥሩ ከዚህ እንደሚያሻቅብ ተመላክቷል። አማራ ድምጽ በበኩሉ የታጋቾች ቁጥር 105 ስለመድረሱ በዘገባው አመልክቷል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply