አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በአርሲ ጀጁ ወረዳ መርቲ ቀበሌ በአማራዎች ላይ ተኩስ ከፍቶ መዋሉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የ…

አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በአርሲ ጀጁ ወረዳ መርቲ ቀበሌ በአማራዎች ላይ ተኩስ ከፍቶ መዋሉ ተገለጸ። አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ ህዳር 20 ቀን 2015 ዓ/ም አዲስ አበባ ሸዋ የመንግስት አካላት ድጋፍ ያልተለዬው አሸባሪው ኦነግ ሸኔ ህዳር 20/2015 ከቀኑ 5 ሰዓት እስከ 7 ሰዓት ድረስ በአርሲ ዞን ጀጁ ወረዳ መርቲ ቀበሌ ቆስጣ በሚባል ሰፈር በከባድ መሳሪያ ጦርነት ከፍቶ ውሏል። በተከፈተው ማንነት ተኮር ጥቃት በአማራ ላይ ከፍተኛ የሆነ ዝርፊያ እና መሳደድ ተፈጽሟል፤ የወራሪው ቡድን አባላትም ለውጊያ የደረሱ ልጆቻችሁን ስጡን እያሉ ህዝቡን ሲያሸብሩ እና እንገላችኋለን እያሉ ሲያስፈራሩ መዋላቸው ተገልጧል። ይህ ሁሉ ሲፈጸም በ500 መቶ ሜትር ርቀት ላይ ባለ ፋብሪካ በጠበቃ ስራ ላይ ያለ መከላከያ ሰራዊት ለህዝቡ ሊደርስ አልቻለም እና አሁን በመርቲ ቀበሌ እና በአዋሳኞቹ ተስፋ ህይወት፣ አጫሞ ፣አዲስ ሂወት ፣መንበረ ህይወት በሚባሉ ቀበሌዎች ያሉ ወገኖች በከፍተኛ ፍርሃት እና ለቅሶ ላይ ናቸው፤ የድረሱልን ጥሪም እያሰሙ ነው። ዘገባውን ለማጠናቀር አስካለ ደምሌ በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ገጿ ጋራችውን መረጃ በምንጭነት ተጠቅመናል።

Source: Link to the Post

Leave a Reply