You are currently viewing “አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ተባባሪዎቹ ባለቤቴን እና ሁለት ልጆቼን በአደባባይ እና በጠራራ ጸሀይ ነጥቀውኛል!”  በምስራቅ ወለጋ ዞን ከሳሲጋ ወረዳ በማንነታቸው የተፈናቀሉት አቶ ይበልጣል ጌት…

“አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ተባባሪዎቹ ባለቤቴን እና ሁለት ልጆቼን በአደባባይ እና በጠራራ ጸሀይ ነጥቀውኛል!” በምስራቅ ወለጋ ዞን ከሳሲጋ ወረዳ በማንነታቸው የተፈናቀሉት አቶ ይበልጣል ጌት…

“አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ተባባሪዎቹ ባለቤቴን እና ሁለት ልጆቼን በአደባባይ እና በጠራራ ጸሀይ ነጥቀውኛል!” በምስራቅ ወለጋ ዞን ከሳሲጋ ወረዳ በማንነታቸው የተፈናቀሉት አቶ ይበልጣል ጌትነት አመሸ! አማራ ሚዲያ ማዕከል/አሚማ… ህዳር 24 ቀን 2014 ዓ.ም አዲስ አበባ ሸዋ ምስራቅ ወለጋ ዞን አማራው በማንነቱ የተነሳ በጅምላ ከሚገደልባቸው፣ ከሚዘረፍባቸውና ከሚፈናቀልባቸው የኦሮሚያ አካባቢዎች አንዱ ነው። አሸባሪው ኦነግ ሸኔ በየቀኑ የንጹሃን አማራዎችን ደም የሚያፈስበት፣ መንግስትና ቀሪው የአካባቢው ነዋሪ አስከሬን እየቆጠረ እና ቀብር እየፈጸመ ወረፋ ከሚጠብቅባቸው የምስራቅ ወለጋ ዞን ወረዳዎች አንዱ ሳሲጋ አንዱ ነው። ከአሚማ ጋር ቆይታ ያደረጉት በምስራቅ ወለጋ ዞን ከሳሲጋ ወረዳ በማንነታቸው ምክንያት የተፈናቀሉት አቶ ይበልጣል ጌትነት አመሸ ይባላሉ። አቶ ይበልጣል ነሃሴ 26 ቀን 2013 እንደ አጋጣሚ ሆኖ በቤታቸው ባልነበሩበት እለት ነበር ድንገት በመምጣት በቤተሰቦቻቸው ላይ አፈና የተፈጸመባቸው። “አሸባሪው ኦነግ ሸኔ እና ተባባሪዎቹ ባለቤቴን እና ሁለት ልጆቼን በአደባባይ እና በጠራራ ጸሀይ ነጥቀውኛል!” የሚሉት አቶ ይበልጣል ሳሲጋ የአማራው የደም መሬት መሆኗን ይናገራሉ። በሳሲጋ ወረዳ አንገር ደዴሳ ከተማ ነሃሴ 26 ቀን 2014 ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ ባለቤታቸውንና ሁለት ልጆቻቸውን በጨካኞች ተነጥቀዋል። ነሃሴ 25 ቀን 2013 የሳሲጋ ወረዳ የፖሊስ ጣቢያን ባቃጠሉና በዘረፉ ማግስት ነበር የአቶ ይበልጣልን 3 ቤተሰቦችን ጨምሮ 6 ሰዎችን አፍነው የወሰዱት። በእለቱ የታፈኑትም:_ 1) ወ/ሮ ወርቅነሽ ምትኩ የተባሉ ባለቤታቸውና 2) ቤቴልሄም ይበልጣል እና 3) በረከት ይበልጣል የሚባሉ ሁለት ልጆቻቸውን ጨምሮ 4) ወ/ሮ ሙሉቀን ጌቴ_የተባሉ የሁለት ልጆች እናት፣ 5) ወ/ሮ ለምለም_ 6) አጫሉ በቀለ (የወ/ሮ ለምለም ባለቤት_በማንነቱ ኦሮሞ) 4 ቤተሰባቸውን እንደበተኑ የታፈኑ። ወ/ሮ ወርቅነሽ ምትኩ 2 ወር ያልሞላው ህጻን ልጅ ጥላ ነው የታፈነችው። አባት አቶ ይበልጣል ጌትነት 2 ወር ያልሞላው ህጻንና የ15 ዓመት ልጃቸውን ይዘው ከአካባቢው በመሸሽ አዲስ አበባ ገብተው በከፍተኛ ችግር እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገልጸዋል፤ እስካሁን አንድም የሰብአዊ እርዳታ ያቀረበላቸው እንደሌለ ተናግረዋል። ከሳሲጋ ወረዳ ታፍነው ወደ ሎምጫ ቀበሌ የተወሰዱ ቤተሰቦቻቸውን እጣፈንታ ጉዳይ ለማወቅ አልተቻለም። አስከሬን አግኝተው እንኳ እምነቱ፣ ወግና ባህሉ በሚፈቅደው አግባብ ለመቅበር አልቻሉም። ለመደገፍ የምትፈልጉና የምትችሉ:_ ይበልጣል ጌትነት:_ አዋሽ ባንክ አካውንት 01320115939000 የስልክ አድራሻ:_ 098 362 3442 ሙሉ ቆይታችንን በአሚማ የዩቱብ አድራሻ ይጠብቁ።

Source: Link to the Post

Leave a Reply